“ወያኔ በኤርትራ ምድር ጦርነት የሚከፍት ከሆነ ጦርነቱ በህውኃትና በዲማክራሲያዊ የኢትዮጵያ ነጻነት ኃይሎች መካከል ነው፡፡” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ምንጮች እንዳሉት በተለያዩ የውስጥ ችግሮች ተወጥሮ የሚገኘው ኢህአዴግ በኤርትራ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው። በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በአካባቢው በሚገኙ የመንግስት ወታደሮች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ቆይተዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶችም እነዚህን ነጻ አውጭዎች ለመቀላቀል ድንበር አቋርጠው እየተጓዙ ነው። ይህ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ስጋት ላይ የጣለው የኢህአዴግ መንግስት፣ በኤርትራ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ለመክፈት ወታደራዊ ልምምዶችንና ዘግጅቶችን በማድረግ ላይ ነው። ሰሞኑን በኦሮምያ ለተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ የኤርትራ እጅ አለበት ሲሉ አቶ ሃይለማርያም መናገራቸው ይታወሳል። ምንም እንኳ የተፈለገውን ያክል የሰው ሃይል ባይገኝም፣ ኢህአዴግ መንግስት ሁለተኛ ዙር ወታደራዊ ምልመላ ለመጀመር ማስታወቂያዎችን በየቦታው ለጥፏል። መከለከያ ሰራዊቱ በከፍተኛ ሁኔታ በዘር ተከፋፍሎ በሚገኝበት በዚህ ወቀት ፣ በኤርትራ ላይ ጥቃት መፈጸም፣ የኢህአዴግን ፍጻሜ ያፋጥነዋል በማለት ምንጮች አስተያየታቸውን አስፍረዋል። በኢትዮጵያ በኩል የሚደረገውን የጦር ዝግጅት በተመለከተ የኤርትራ መንግስት የሰጠው መግለጫ የለም።

በተያያዘ ዜና ወያኔ መራሹ አንባገነኑ የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ ጋር ድንገተኛ ጦርነት እንደሚጀምር እየተነገረ ነው፡፡ አይጀምርም እንጂ የሚጀምር ከሆነ እሱ ጦርነቱን ከሚያሸንፍ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይቀላል፡፡

“ወያኔ በኤርትራ ምድር ጦርነት የሚከፍት ከሆነ ጦርነቱ በሻቢያና በህውኃት መካከል አይደለም፡፡ ጦርነቱ በኤርትራ መንግስትና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል አይደለም፡፡ ጦርነቱ በወያኔና በዲማክራሲያዊ የኢትዮጵያ ነጻነት ኃይሎች መካከል ነው፡፡”
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
የአግ7 ሊቀመንበር

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to “ወያኔ በኤርትራ ምድር ጦርነት የሚከፍት ከሆነ ጦርነቱ በህውኃትና በዲማክራሲያዊ የኢትዮጵያ ነጻነት ኃይሎች መካከል ነው፡፡” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

  1. abe says:

    Banda ,

    Just eat your double burger what do you know about war. Why are you hiding under shaebia skirt in DC ? Weren’t you supposed to be in Asmara?

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: