የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አዛዦች በአዲስ አበባ ስብሰባ አካሄዱ፡፡ ስብሰባው ያለምንም ውጤት በግጭት ተቋጭቷል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አዛዦች በአዲስ አበባ ከየካቲት 9 እስከ 12 2008 ዓ.ም የተሰበሰቡ ሲሆን የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የፀጥታ ሁኔታ እና የአባላት መክዳት እያነሱ ከተወያዩባቸው አጀንዳዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በስብሰባው ላይ የአማራና የኦሮሞ ተወላጅ አዛዦች “እኛ ከእናንተ የተሻለ የትምህርት ደረጃና ልምድ እያለን ሁሉንም ቦታ ጠቅልላችሁ ይዛችሁት ተገቢው ቦታ አልተሰጠንም…” በማለት ህወሓቶችን ልካቸውን ነግረዋቸዋል፡፡

ህወሓቶች በፌደራል ፖሊስ ተቋም ውስጥ ባሰፈኑት ዘረኝነት ምክንያት ሰራዊቱ በመፍረስ ላይ እንደሚገኝ ስብሰባው ላይ በተደጋጋሚ ተወስቷል፡፡ በውይይቱ ላይ ተቃውሟቸውን ያሰሙ የኦሮሞና አማራ ተወላጅ አመራሮች ከህወሓቶች “የእናስራችኋል” ማስፈራሪያ ደርሷቸዋል፡፡

በመጨረሻም ስብሰባው ወደ ለየለት ንትርክና አምባጓሮ በማምራቱ አብዛኞቹ አዛዦች እንዲበተኑ ተደርገው ውይይቱ በጥቂት ዋና፣ ዋና አመራሮች ለተጨማሪ ጊዜ ተካሂዷል፡፡ የፌደራል ፖሊስ አደረጃጀት ሊፈርስ እንደሚችልም ጭምር ጭምጭምታ ተሰምቷል፡፡

በተያያዘ ዜና የሚከዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥር አሁንም ከቀን ወደ ቀን እየናረ መምጣቱ እየተነገረ ነው፡፡ በጎንደር ብቻ ቢያንስ በቀን 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት እንደሚከዱ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አዛዦች በአዲስ አበባ ስብሰባ አካሄዱ፡፡ ስብሰባው ያለምንም ውጤት በግጭት ተቋጭቷል፡፡

  1. Pingback: የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አዛዦች በአዲስ አበባ ስብሰባ አካሄዱ፡፡ ስብሰባው ያለምንም ውጤት በግጭት ተቋጭቷል፡፡ - EthioExplorer.com

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: