መሬቱ የእኛ የኦሮሞዎች ከሆነ መሬታችን ለቀዉ መዉጣት ያለባቸዉ ኦህዴድና ህወሃት ናቸዉ የብሔር ጠላት የለንም!
February 20, 2016 Leave a comment
የመላዉ ኢትዮጵያ ህዝቦች ቀንደኛ ጠላት የሆነዉ የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን በኦሮሞና በተለይም በአማራዉ ብሔረሰቦች መካከል የእርስ በእርስ ፍጅት ለመፍጠር በብርቱ እየሰራ ይገኛል ተስማምተዉና ተከባብረዉ በሚኖሩ በነዚሁ ብሔረሰቦች መካከል ጸብ ለመጫር በሚችልበት መልኩ እንዲሰራ ከልዩ መረጃ ቢሮ በህወሃት የዘርፍ ካድሬ አባላቶች አማካኝነት የለኦህዴድ በተሰጠ ትእዛዝ መሰረት አማራዉ ኦሮሞን ሊያጠፋ ነዉ ትጥቅ ይፍታ! ኦሮሞዉ አማራን ሊያጠፋ ነዉ ትጥቅ ይፍታ! በሚል መነሻ ሰበብ የክልሉ መከላከያ ሰራዊቶች በደቡብ ምእራብ ሸዋ ጉሮ ወራዳ ከትናንት ጀምሮ የኤሌክትሪክ ማብራት እንዲጠፋ ተደርጎ ወረዳዋ ሙሉ በሙሉ በኦሮሚያ ፖሊስ ተወራ እንደምትገኝና ህዝቡ ላይ ከፍተኛ ፍራቻ ማደሩን ምንጮች ገልጸዋል በተጨማሪ በሌሎችም የዙሪያ ቀበሌ አካባቢዎች በኦፒዲዮ ከፍተኛ አመራሮች የታገዘ የትጥቅ ማስፈታት ስራ እና የማጣላት እቅዱ ከትናንትናዉ እለት ጀምሮ ተግባራዊ ሲሆን በደቡብ ምእራብ ሸዋ በአማያ ወረዳ የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸዉ በሚል ሰበብ የአማራ እና ኦሮሞ ገበሬዎችን ሆን ብሎ ማፈናቀሉ ዛሬ ተጀምሯል ኦህዴድን ከፊት በማስቀደም ከሗላ እንደ ጦስ ዶሮ የሚከተለዉ ህወሃት በአጠቃላይ ሐገሪቱ ላይ የተቀጣጠለዉን ህዝባዊ አብዮት በመፍራት ምክንያት የእርስ በእርስ ግጭት ለመቀስቀስ በከፍተኛ ሁኔታ እየተገበረ ይገኛል።
ከስፍራዉ ያነጋገርናቸዉ አንድ የአማራ ብሔር ተወላጅ ኢትዮጵያዊ እንደገለጹልን ” አብረን ተከባብረንና ተዋደን እንዲሁም ተዋልደን በምንኖርበት ሐገር ላይ ልጅህ ሊገድልህ ነዉ አባትህ ሊያጠፋህ ነዉ እያሉ ማደሪያ አሳጡን ትጥቅ ካልፈታችሁ በሚል ሰበብ ቤታችን ኢየተፈተሸ ነዉ የሚደርስልን አካል የለም ፈጣሪ ግን ይፍረድ በማሌት ሐዘናቸዉን ሲገልጹ ” ሌላኛዉ በግብርና ስራ ላይ የሚተዳድደር ግለሰብ ደግም ” ይህ መሬት የኦሮሞ እንጂ የአማራ አይደለም ከእርስትህ አማራና ሌሎችን አስወጣ በሌሎች ክልሎች እንዲህ እየተደረገ ነዉ እያሉ አስቸገሩን እዉነት መሬቱ የእኛ የኦሮሞዎች ከሆነ መሬታችን ለቀዉ መዉጣት ያለባቸዉ ኦህዴድና ህወሃት ናቸዉ የብሔር ጠላት የለንም ሲሉ በከፍተኛ ቁጭት መናገራቸዉን ምንጫችን አክሎ ገልጿል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
ጉድሽ ወያኔ
