በትግራይ ክልልና ኣማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን ድርቁ ባስከተለው ረሃብ የሰውና የእንስሳት ሂወት እየተቀጠፈ ነው።

ድርቁ ለመከላከል ተብሎ እየመጣ ያለው የእርዳታ እህልና እርዳታ ጠባቂ ህዝብ ቁጥር ስለማይመጣጠን፣ የመጣው እርዳታ ከከፍተኛ ባለ ስልጣናት እስከ የቀበሌ ካድሬዎች እየዘረፉትና ኢ_ፍትሓዊ በሆነ መንገድ ስለሚከፋፈል እርዳታው የህዝቡና እንስሳቱ ሂወት ከሞት ሊታደግለት ኣልቻለም።

በሰው ሂወት እየደረሰ ያለው ኣደጋ በህፃናትና ኣረጋውያን የሚብስ ሲሆን ከእንስሶች ደግሞ በፍየሎችና በጎች የበለጠ ኣደጋ ኣስከትለዋል።

በረሃብ እየሞተ ያለው የሰው ስምና ፎቶ በፌስቡ ገፅ መለጥፍ የሚቻል ቢሆንም ለቤተሰቦቻቸው ሞራል ሲባል ኣይበረታታም።

በምስሉ የምታዩት የሞቱ በጎች ምስል በኣፅቢ ወንበርታ ወረዳ ሩባፈለግ የተባለ ቀበሌ ኑዋሪ የሆኑት የኣቶ ሕድሮም ሃይለ ስላሴ በጎች ናቸው። የወረዳዋ እንስሳት በተመሳሳይ ሁኔታ በየቀኑ በረሃብ እየረገፉ ይገኛሉ።

በየወረዳው የሚኖሩ የዓረና ኣባላት ሁለት ጨካኝ ሃይሎች ጎሮሯቸው ኣንቀው መልኣከ ሞት እየጠሩላቸው ይገኛሉ።

እነዚህ ጨካኞች ህወሓትና ድርቅ ሲሆኑ “ታሪክ ራሱን ይደግማል” እንደሚባለው የትግራይ ህዝብ በ77ቱ ድርቅ ግዜ ድርቅና ሻዕብያ ግምባር ፈጥሮው እንደፈተኑት ኣሁንም ህወሓት የሚቃወማቸው ህዝብ ለማንበርከክና ለመበቀል የወቅቱ ድርቅ እንደመልካም ኣጋጣሚ ተጠቅሞ በሂወታቸው እየመጣ ነው። እርዳታ የጠየቀ የዓረና ኣባል “ዓረና ይስጣቹ” የሚል ምላሽ ያገኛል።

እንደ ህወሓት ውሳኔ “ረሃቡ ለመቋቋም ሲሉ ዓረናዎች በእግራችን ይወድቃሉ፣ ይለምናሉ፣ ኣለበለዝያ ሂወታቸው ያጣሉ” በሚል ስሌት መላ የትግራይ ኑዋሪ የዓረና ኣባላት ከእርዳታ ውጭ ኣድራጓቸዋል።

ይኸው… ! የዓረና ኣባላት ለሆዳቸው ሲሉ ወደ ህወሓት ኣልገቡም። ህወሓት በዓረና ኣባላት ላይ ካሰበችው ሴራ በተጨማሪ ያላት ሙሰኛ ባህሪ እርዳታው በየ እርከኑ እየተዘረፈ እርዳታው ለተረጂው ሳይደርስ በመቅረቱ ሰውና እንስሳ በረሃብ እየሞተ ነው።

ህወሓትም እንደ ኢሉሙናቲ “ጠላቶቼ” ብሎ የፈረጃቸው የዓረና ኣባላት፣ ወደ ስልጣን እንዳላስመጣው እየተጠየፈው እየመጣ ያለው የትግራይ ህዝብና የህዝቡ እንስሶች ሲሞቱ ደስ እየተሰኙ ነው ባይባልም ከቁብ ኣልቆጠሩትም።

የተወደዳቹ ኢትዮጵያውያን ሆይ……! መንግስት በጥጋብ ልቡ ሲደነድንና ህዝቡን ቢረሳ እናንተስ እንዴት በወገናቹ ርሃብና ሞት ሆዳቹ ኣይባባም?

የህወሓትና ካድሬዎችና ደጋፊዎች የእርዳታው እህል ወደ ህዝቡ እየደረሰ እንዳልሆነ እኔን ካላመናቹ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባልና የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኣስተዳዳሪት ወይዘሮ ያለም ፀጋይ በድምፅ ወያነ ያለፈው ምስክርነት እንዴት ኣታምኑም?

የብኣዴን ዋግህምራ ዞን ካድሬዎችና ኣባላት ወገኖቻቹ በረሃብ እያለቁ ነው። ተሰድደው መጥተው የመቐለ ጎዳናዎችም እያጥለቀለቁዋት ነውና ስለ ህዝባቹ ብላቹ ኣስፈላጊ መላና ድጋፍ ኣድርጉላቸው።

በሌሎች ክልሎች ያለው የረሃብ ሁኔታ መረጃ ባለ ማግኘቴ ላካትተው ኣልቻልኩም።

ስለዚ የህዝባችን ችግር እንጋራ፣ ሂወቱ እንታደግለት፣ እንስሶቹም እናትርፍለት፣ ይሄ ድርቅ ለፖለቲካዊ ትርፍ ተብሎ በዓረና ኣባላት ላይ እየደረሰ ያለው ማግለል የሞት ፍርድ ስለሆነ በህብረት እናቁመው።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: