አባ ማትያስ የጠሩት ስብሰባ ሳይሰበሰብ ተቋጨ፡፡

አቡነ ማትያስ የጠሩት ስብሰባ ፓትርያርኩ በክርስቶስ ወኪልነት መከበር አለባቸው በሚል አምባገነናዊነትና ካቶሊካዊ አስተምህሮ ተደመደመ፡፡ ጤነኛ ተሰብሳቢዎችን ሳይቀር ባስገረመ ሁኔታ ከብፁዓን አባቶች ጋር መወያየቱን ትተው በሌላቸው ሥልጣን የመምሪያ ሓላፊዎችንና የኮሌጅ ተወካዮችን የሰበሰቡት ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳንን በተለመደው ሁኔታ በመክሰስ መድረኩን ለተሰብሳቢዎች ከፈቱት፡፡ ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳንን ለመክሰስ ይጠቅመኛል ብለው ያሰቡትን ምክንያትም ሰበብም (እውነቱንም ውሸቱንም) ደርድረው አንድ ነገር መባል አለበት ሲሉ ማኅበረ ቅዱሳንን እንደ አባት ገዳይ የሚያዩት ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃና አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የተለመደ የስቀሉልን አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ አባ ሠረቀ የመምሪያው ሓላፊ ሳሉ ብዙ ጊዜ ሞክረው አልሳካላቸው ያለውን የማኅበሩን ሚዲያዎች ማዘጋት ይህን ግርግር ተጠቅመው ለመቀዳጀት አስበው ነበር፡፡ ግን እንዳሰቡት የማኅበሩን ሚዲያዎች መዝጋት የስብሰባው ውሳኔ ሳይሆንላቸው ቀረ፡፡ ተሰብሳቢዎች ሁሉ የሚሉትን አሉ፤ የሚሳደቡት ተሳደቡ፣ የሚራገሙት ተራገሙ፣ የሚታዘቡት ታዘቡ፡፡ ቤተ ክርስቲያን አሁን ላለባት ችግር ሁሉ ተጠያቂው ማኅበረ ቅዱሳን ነው ተባለ፤ ሌላም ሌላም፡፡
በመጨረሻ ግን ሁሉም ከልኩ አያልፍምና ማኅበሩ “የክርስቶስ ወኪል” ለሆኑት ለቅዱስ ፓትርያርኩ ደብዳቤ መጻፉ ስሕተት ስለሆነ ይቅርታ ይጠይቅ የሚል ኑፋቄያዊ ውሳኔ ላይ ደረሱ፡፡ ፓትርያርኩን ብቻ ሳይሆን ኮሌጆችም ላይ የጻፈውን ጽሑፍ ያስተባብል አሉ፤ ያለ ሥልጣናቸው በፍርድ ወንበር ላይ የተቀመጡት ተሰብሳቢዎች፡፡ ዐውቆ የተኛ ለትንሣኤም አይነቃ እንደሚባለው ክፉ መካሪዎቹን ከጎኑ ማራቅ ያልቻለ መሪ ሁልጊዜም ውሳኔው እነዲህ ዐይነት ነው፡፡ በሰዎች ሕይወት ላይ የማዘዝ ሥልጣን ያላቸው የሚመስሉ ባለጊዜዎችን የሚፈሩ ፈርቶ አደሮች እንደ ሱፍ አበባ ወዳልዳመነበት ሲዟዟሩ ይታያሉ፡፡ ሥጋችሁን የሚገድሉትን አትፍሯቸው የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ያገኘኝ ሁሉ ይገድለኛል በሚለው የቃየል ቃል ተተካ፡፡ የትግል መጋዝ ሲሔድም ሲመለስም ይቆርጣል እንደሚባለው እነ ንቡረ እድ ከእነዚህ ሆድ አደሮች ጋር ተሰብስበው ማኅበሩን ካጠፉ በኋላ ተሰብሳቢዎችን ደግሞ ሲመለሱ ያበሯቸዋል፡፡ ሆዳም ሰውና ጓያ ነቃይ የፊት የፊቱን እንጂ ሩቅ ማየት አይችልም፡፡ ጌታ ሆይ የቤተ ክርስቲያን ምነው ዓርብዋ በዛ፡፡ መቼ ይሆን እሑዷን የምታሳየን፡፡ “ተባርዮ የማያስቀር እግዚብሔር መፍቀሬ ሃይማኖት ራትዕ ንጉሥ አስነሣላቸው” የሚለው ቃል በእኛም ዘመን ተፈጽሞ የምናየው መቼ ይሆን? አሁንማ የንጉሡ ቀርቶብን አባትም አጣን፡፡ ለሚመጣውም አባት ደኅና መሆን ዋስትና የለንምና ሌላ አባት ስጠን አንልህም፣ ያሉትን ልብ ስጥልን ወይም የሚሆነንን ከእኛ በላይ አንተ ታውቃለህና ለቅድስት ድንግል ማርያም አሥራት አድርገህ ለሰጠሃት ለአገራችን እና ለቅዱሳን ስለ ገባህላቸው ቃል ኪዳን ብለህ ጥሩ አባት ስጠን

e6165-bemjdn4cmaamqwj

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: