«ለአፍሪካዊያን ዲሞክራሲ ቅንጦት ነው፣ ኃይሌ ገብረሥላሴ።

«ለአፍሪካዊያን ዲሞክራሲ ቅንጦት ነው፣ የሚገባቸው ዲሞክራሲ ሳይሆን መልካም አስተዳደር ነው።»

ኣለ አሉ… ፖለቲሺያን ኃይሌ ገብረሥላሴ። “ፖለቲሺያን” ስል እያፌዝኩት ወይም እያሽሟጠጥኩ አይደለም። ሁላችንም እንደምናውቀው ኃይሌ ኢትዮጵያንና እኛን ሕዝቦቿን በድል ካኮራበት ሙያው ወደ ፖለቲካው ተገብቷል። መብቱ ነው!

ግና ገና ከጅምሩ በፖለቲካው መክሸፍ ሲያበዛ እየታዘብን ነው። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዙሪያ የሚሰጣቸው አስተያየቶች በእዝላልነት ይሁን ወይም ፖለቲካውን ባለመረዳት አላውቅም ብዙውን ጊዜ ግራ የሚያጋቡ ናቸው። … ዲሞክራሲ በሌለበት አኳኋን መልካም አስተዳደርን እንዴት ማስፈን እንደሚቻል አይገባኝም! ኃይሌ ለፖለቲካዊ ነገሮች በጣም የፈጠነ ይመስለኛል፤ ሰከን ረጋ ብሎ ብዙ ጥናቶችን ቢያደርግ ብዙ ጥሩ ነገሮችን አውቆ ማሳወቅ በቻለ ነበር። ለጥናት የሚሆን በቂ ባጀት ባይኖረውም ቅሉ smile emoticon

ሌላውና ሁሌም ሳስበው የሚገርመኝ ነገር ደግሞ የልጆቹ አፈ ፈረንጅነት ነው። እስቲ አስቡት ኃይሌ ተወዳድሮ አሸንፎ የአገሪቱ መሪ ሲሆንና EBC ዶክመንተሪ ሲሰራለትና የልጆቹ ቃለ ምልልስ እየተተረጎመ ሲነገረን wink emoticon … ምናለ እንደው አማርኛው እንኳ ቢቀር ኣፋን ኦሮሚኛ ቢያስተምራቸው?? … እስከማውቀው ድረስ ልጆቹ ኦሮሚኛም አይችሉም።

ግን! ሁሌም እንደምናከብርህ፣ ሁሌም እንደምንኮራብህ፣ ሁሌም እንደምንወድህና የምንጊዜም ጀግናችን እንደሆንክ ትላንትም መስክረናለን ዛሬም እንመሰክራለን ነገው ደግመን እንመሰክራለን።

ይቺን የፖለቲካ ነገር ግን እንደጫማህ ወዲያ ወደ ቆጡ ብትሰቅላትና ዝም ብለህ ቤተስኪያን እየሳምህ ብትኖር ደስ ይለኛል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to «ለአፍሪካዊያን ዲሞክራሲ ቅንጦት ነው፣ ኃይሌ ገብረሥላሴ።

  1. kilo Mamo says:

    Haile’s children, if they do not know Orominga, what the problem?. since Oromiya is belong to all of us. but don’t forget Haile is grow up and living in Oromiya. Many of confused Diaspora said
    “not oromiya, since we are living in America, we are American”. It is correct, but their kids not to speak or learn English, so why Haile’s kids don’t want to learn or speak orominga. This is the MAIN PROBLEM OF the people called them self Ethiopia. Like Abe Tokichaew.

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: