ህሊናዬ የመራኝ ነገር “ፈሪ አድርጎ ለተመለከተኝ ብረት የማንሳት ልብ እንዳለኝ ጭምር አሳይቻለሁ!! “

“ምንም የሚሰማኝ “ነገር የለም፡፡ ህሊናዬ የመራኝ ፈሪ አድርግው ለተመለከቱን ቡድኖች እነሱ የደፈሩት እኔም እንደማላንስ ብረት የማንሳት ልብ እንዳለኝ አሳይቻለሁ፡፡)))) ወደዛ ለመሄድ የገፋን ወያኔ ነው፡፡ ምንም ወንጀል የለብኝም፡፡ ጥፋታችን ሀገራችንን ማሰባችን ካልሆነ ብረት ማንሳት ህጋዊ የሚሆነው ለወያኔ ብቻ ያደረገው ማነው? የፖለታካው ጨዋታ በእነሱ ቁመና ታጥሮ ሰላማዊ ትግል እንደማይቻል (አንድነትን) አፈረሰ ሰልፍ በወጡ ዜጎች በገዳይ ሰራዊቱ ጥይት በመተኮስ እየገደለ ሰላማዊ ትግል አያዋጣም ያለን እራሱ ወያኔ ነው፡፡ በእርግጥ “እኛ መስማት ተስኖን እንጂ ከነገሩን ቆይቷል፡፡
“ህግ አክብረን በሰላሙ መንገድ መታገል አመራጭ ስናደርግ የለም “ሂዱ መንገዱን ጨርቅ /ሲሉን “ምን ለማለት እንደፈለጉ ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡ ስለዚህ እኔ የአቋም ለውጥ ማድረጌ አንዳች ስህተት አልሰራሁም፡፡ ፓርቲያቸውን ተቀምተው በጠራራ ፀሐይ የተደበደቡ ጓዶች መከላኪያ ምስክሮቻችን ናቸው፡፡ መንግስት እራሱ ለእኛ መከላኪያ መሆን አለበት ትክክል ስለሆንን/ ዛሬ ሴቶቹ እስር እና ድብደባ ሳይበግራቸው ወንዝ ተሻግረው ሊዋደቁ ግንባር ቀደም ተሰላፊ ሆነዋል፡፡ ከእስር ተፈታ ወንድሟን ተሰናብታ ንገረው” ነጻ የማወጣህ እኔ “ነኝ እያሉ ብረት ለማንገት ወንዝ ተሻጋሪ ሆነዋል፡፡ “ይሄ ብሶት ነው እኛን ያስገባን/ መገፋት በስርዓቱ ተስፋ ማጣት ስትጀምር የምትወስደው ጉልበት ወደመጠቀም ደረጃ ትገደዳለህ እውነቱ ይሄ ነው፡፡ በዚህ ከተቃኘ ጥፋተኛው እኔና ጓዶቼ ሳንሆን በገዛ ሀገራችን ተስፋ አሳጥተው እንደ ውሻ የቆጠሩን ወያኔና ማሕበርተኞቹ ናቸው፡፡ በሰላማዊ ትግል እየደከምን የቆየን ሰዎች ነን/ በእርግጥ ብዙ ጓዶች ዋጋ ከፍለውበታል እየከፈሉም ይገኛል፡፡ ነገር ግን በእነዚህ እውነተኛ ታጋዮች የተገነባ ድርጅት እንዲኖር ማድረግ አልተቻለም፡፡ እስር ቤት መጥቶ ጓዶችን ለማየት የሚከብደው ብዙ አለ፡፡ ሀገሩን ብትሰድብ ምንም የማይመስለው ስትተቸው ግን ጭራ የሚሆን ፓርቲ እንደ አክስዮን የገዙት ይመስል እሱ ትላንት መጥቶ ለምን? ይሉሀል/ በእንዲህ ያለ ግለሰቦች የተመሰረተ በውስጥና ውጫዊ ገመድ ጉተታ የተተበተበ ተቋም ለውጥ አያመጣም፡፡ በግለሰቦች ስብዕና ለታይታ ለምርጫ እራሳቸውን ከካቡ የውስጥ መንጋ ነጻ የሆነ ጠንካራ ድርጅት እንዳይኖር ወያኔ በውጪ አፋኝ ተቋሞቹን እየተጠቀመ ሲያዳክም በውስጥ የእራሱ ጉዳይ አስፈጻሚ ትግሉን ገድለውታል፡፡
(( አንድነት ሲፈርስ ያኔ ሰማያዊ ፈርሷል፡፡)) አንድነት ያልተወዳደረበት ምርጫ ሰማያዊ ምን ይበጀዋል? ይሄን ማገናዘብ ቀላል ቢሆንም የውስጥ ሀይሎች በሚፈጥሩት ማነቆ አስካሁን ትግሉን ሲጎዱት እየተመለከትን ነው፡፡ ይሄ በሆነበት የጨዋታ ሜዳ ወያኔ በፍርሀቱ ልክ ትግሉን ሲዘጋው የራሳችንን አማራጭ መውሰድ ከሞራልም ከህሊና ሚዛናዊነት ቢታይ ትክክለኛ ውሳኔ ነው፡፡ ጥፋተኛ ከተባለ ሁሉን በጉልበት የተቆጣጠረው ስርዓት ብቻ ነው፡፡
// ብርሃኑ ተ/ያሬድ)

Dudi Andargachew's photo.
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: