የጀግናው ወልቃይቴ ሙቀት ራያም እየተፋፋመ ነው!

ሁለቱም ሀገሪቱ የምትተማመንበት ድንግል መሬት፤ለም አፈር፤ከፍተኛ የቀንድ ከብት ክምችት ያለባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ራያዎችም አንደ ወልቃይቶች የተመሰከረላቸው ጀግኖች ናቸው፡፡ራያ በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ አካበባ በወሎ ክ/ሀገር ይገኛል፡፡ወልቃይት በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ደቡብ ምዕራብ አካበባ በጎንደር ክ/ሀገር በወገራ አውራጃ ይገኛል፡፡ ራያም ወልቃይትም 1984 ዓ.ም በትግሬ ነፃ አውጭ ቡድን በወረራ ተይዘዋል፡፡
ሰሞኑን የወልቀይት ጀግኖች በማንነታቸው ላይ የተጫነውን ትግሬነት አራግፈው ዐማራ መሆናቸውን አውጀዋል፡፡ለደንቡ ቢሆንም በይስሙላው የመንግስት ተቋም አቤቱታቸውን እያሰሙ ነው፡፡ለአቤቱታ በወጡ ወልቃይቶች ላይ እብሪተኛው የትግሬ መነግስት የአፈና እና የእስራት ርምጃ ወስዷል፡፡ምንም እንኳን የሽማግሌዎች መታሰር የወልቃይትን ዐማራነት ባያስቆመውም፡፡
በዚህ በወልቃይት ጀግንነት የተበረታታው የወፋላ፤የራያ አካባቢ ኗሪ እርሱም በግድ ከተጫነበት የትግሬነት ቀንበር ለመውጣት ከፍተኛ ምክክር እያደረገ ሲሆን ሰሞን ከወልቃይት ለመጡት የሕዝብ ተወካዮች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ መሆናቸውም ታውቋል፡፡
አንድ የስልሳ ዓመት የራያ እና የወፍላ አዛውንት ለአካባቢው ህዝብ እንዲህ የሚል መልክት አስተላልፈዋል፡፡”ከወልቃይት የሕዝብ ተወካዮች አንድም ሰው ቢሆን በወያኔ ርምጃ ከተወሰደበት ሁሉም ሰው ይህንን ርምጃ ለሚያካክስ ፈጣን ምላሽ ዝግጁ እነዲሆኑ” ጥሪ አድርገዋል፡፡
አሁን ባለው የወልቃይ ሙቀት ራያም በቅርብ የዐማራነት ማንነቱን እንደሚያስመልስ አሁን የሚታዩት ምልክቶች ጠቋሚ ናቸው፡፡
እኛ መች ፈለግነው የትግሬን ሰው ጠጅ፤
እየበጠበጡ ይግቱናል እንጅ ፡፡ የሚል የቁጭት ቀረርቶ፤ፉከራ እና ሽለላ ጮህ ብሎ እያሰተጋባ ነው፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: