“ኢትዮጵያዊቷ የ23 ዓመት ኩዌታዊ ወጣት ነፍስ አጠፋች ” ተባለ

ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ የ23 ዓመቷን ፋጢማ የተባለችን ኩዌታዊ የአሰሪዋን ልጅ ገድላ ራሷን ለማጥፋት ስትሞክር በፖሊስ መያዟን የኩዌት መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል ። ኩዌት ውስጥ አል አንድሉስ በተባለ መንደር ፈጸመች የተባለችው ኢትዮጵያዊት በጩቤ ግድያ ከፈጸመች በኋላ የራሷንም አንገት በመቁረጥ ባደረገችው ሙከራ በጸና ቆስላ በአሁኑ ሰአት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሳባ በሚባል ሆስፒታል ህክምና በማግኘት ላይ መሆኗ ታውቋል !

ኩዌት ታይመስ የተባለው ጋዜጣ እንዳስታወቀው የተገደለችው ኩዌታዊ ኮረዳ በኩዌት የደህንነት መስሪያ ቤት የምርመራ ሰራተኛ እንደነበረች መረጃ እንደደረሰው ቢያስታውቅም መረጃው አለመረጋገጡን ጋዜጣው ጠቁሟል ። ጋዜጣው ከዚህ ጋር በማያያዝ ኢትዮጵያዊቷ እህት ይህን ግድያ ለማደረግ ምን እንዳነሳሳት አለመታወቁን ጠቁሟል ።

በግድያው ዙሪያ ያነጋገርኳቸው በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግድያው ከቀትር በኋላ መፈጸሙን እንደሰሙ ፣ ጉዳዩን ለኢንባሲ ማሳወቃቸውን ሲጠቁሙ የግድያው ዜና በኩዌት ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን በሰፊው እየየሰራጨ መሆኑን ገልጸውልኛል ። ኩዌት ነዋሪ የሆነው የመረጃ ታማኝ ምንጭነቱ የምናውቀው Nezar Dage ግድያውን ተከትሎ በፊስ ቡኩ ባስተላለፈው መልዕክት እንዲህ የሚል ይገኝበታል” …የተፈጠረው አሳዛኝ አደጋ ሁላችንንም ያሳዘነ እና ድጋሚ አንገት የሚያስደፋ ነው ። የግድያውን ዜና ተከትሎም እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አግባብ ያልሆነ ነገር እየተወራ ነው በጅምላ የኢትዬጵያኖችን ስም እያጠፉ ነው ።
ዋነኞቹ ደሞ ምንም ተጨባጭ መረጃ የሌላቸው እና ስለኢትዬጵያ አንድም የማያውቁ ኩዌት ውስጥ ያሉ የሶሻል ሚዲያዎች ናቸው ” ያለው ኒዛር በመቀጠል ” እስካሁን የግድያው መንስሄ ምን እንደሆነ ባልታወቀበት እና ባልተጣራ መረጃም ብዙ አሉባልታ እየተናፈስ ነው ” በሏል ።

በመጨረሻ ኒዛር በተለይም በሰው ቤት ተቀጥረው ለሚሰሩ እህቶች ባስተላለፈው መልዕክት እንዲህ ሲል ምክሩን ለግሷል ” … በቤት ውስጥ የምትስሩ እህቶች ምንም ሳትረበሹ በምትስሙት ወሬም ሳትደናገጡ እንደበፉቱ ስራችውን በአግባቡ ስሩ ። አላስፈላጊ ክርክር እስጠ ገባም በምንም ታምር ከአስሪዎቻችው ጋር አትግጠሙ ለምታደርጉት ነገር ትዕግስት ይኑራችው !” ሲል ያለውን ሁኔታና ምክሩን ጭምር አስተላልፏል !

ነቢዩ ሲራክ

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: