ኦህዴድ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ነው::

በኦሮሚያ የአምባገነኑ የህዋሀት መንግስት ተላላኪ ሆኖ የግፍ ስርዐቱን እያስቀጠለ የሚገኘው ኦህዴድ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ነው፡፡ የድርጅቱ ባለስልጣናትም ከዛሬ ነገ ተነሳን፣ ወደ እስር ቤት ተወረወርን እንዲሁም ለስደት ልንገፋ ይሆን? ጭንቀት ላይ ናቸው፡፡ ኦህዴድ የኦሮሞን ህዝብ እንደማይወክል፣ የህዋሀት ተላላኪ ለመሆኑ እና እጅግ ደካማ ድርጅት ለመሆኑ ህዝቡ ብቻ ሳይሆን የድርጅቱ የበላይ አመራሮች ሳይቀሩ ማመን ጀምረዋል፡፡
ድርጅቱ እና የበላይ አመራሮቹ በአንዲት እጅግ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ በምትገኝ የህዋሀት ጋዜጠኛ ሳይቀር “ሌቦች፣ ዘራፊዎች እና ሙሰኞች” ተብሎ ሲዘለፉ ምንም ማድረግ ያልቻሉ ሲሆን፤ አሁንም በዝቅተኛ ደረጃ በሚገኙ ጋዜጠኞች ወሬ እየተፈበረከ ሆን ተብሎ እንዲጨነቁ እየተደረገ ነው፡፡
በቅርቡ እንኳን “ በዝግ ስብሰባ በከር ሻሌ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሆኑ፤ በከር ለህዋሀት ወሬ በማመላለስ ክህሎታቸው እንዲሁም ህዝባቸው አንዲያልቅ በሚያሳዩት ተባባሪነት ‘ተከስተ’ የሚል ቅፅል ስም ተስጥቷቸዋል” እንዲሁም አባዱላ ገመዳ፣ ሙክታር ከድር፣ ለማ መገርሳ፣ ዳባ ደበሌ እና አብይ አህመድ የተባሉ ከፍተኛ የኦህዴድ አመራሮች ከስልጣናቸው እና ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው ተነስተው አስር ቤት ሊወረወሩ ነው የሚሉ ዜናዎች እየተፈጠሩ ባለስልጣናቱ እንቅልፍ አልባ ሌሊት እንዲያሳልፉ እየተደረገ ነው፡፡
እነዚሁ የኦህዴድ አመራሮች ወሬውን የሚፈበርኩት እና እንዲናፈስ በዝቅተኛ ደረጃ ለሚገኙ የህዋሀት ጋዜጠኞች የሚሰጡት የህዋሀት ከፍተኛ አመራሮች ናቸው በማለት የተጨነቁ ሲሆን፤ ውሳኔውን ወደ ተግባር ለመለወጥ ይህን ብንወስን ምን ይፈጠራል? የሚል የቅድሚያ ምዘና በህዋሀት በኩል እየተሰራባቸው ሊሆን እንደሚችልም ጠርጥረዋል፡፡

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: