በደቡብ አፍሪካ አንድ ኢትዮጵያዊ በዘራፊዎች ተገደለ

በደቡብ አፍሪካ ቢያንስ በአንድ ቀን ዉስጥ አንድ ወይም ሁለት ወገኖቻችን በዘራፊዎች ወይም እርስ በእርስ በሚነሳ ጸብ ወይም ተንኮል ሳይገደል አይዉልም።
ባለፈዉ ሳምንት እጅግ አሳዛኝ የሆነዉ ክስተት ቴምቢሳ ላይ የተፈጸመ ሲሆን ይህዉም የአጎቱን ልጅ ሰርግ ሰርጎ ነገ ሰርጉ ላይ መገኘት ሲኖርበት ዛሬ የተገደለዉ አነሞ የተባለዉ ወንድማችን ብዙዎችን አሳዝኖአል በወቅቱ አነሞ መኪናዉ ዉስጥ ሊገባ ሲል ዘራፊዎች ደርሰዉ መሳሪያ ግንባሩ ላይ ደቅነዉ መኪናዉን እንዲያስረክባቸዉ ሲጠይቁት ፍቃደኛ ሆኖ ሊሰጥ ባለበት ወቅት ላይ ሌላዉ ኢትዮጵያዊ ጓደኛዉ ተመልክቶ መሳሪያ አዉጥቶ ዘራፊዎቹ ላይ በመተኮሱ ሌቦቹ አነሞ ላይ ጥቃት የፈጸሙ ሲሆን ህይወቱም ያኔዉኑ አርፋለች።በመሆኑም ባሳለፍነዉ ሳምንት እሁድ የአነሞ የአጎት ልጅ በሐዘኑ ማግስት የሰርግ ስነ ስረቱን በጸጋ ተቀብሎ ሊያሳልፍ ችሏል።
በተለያየ ስፍራ እየደረሰ ያለዉ ግድያ እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት ላይ ሌንዲላ በተባለዉ እስር ቤት በመኖሪያ ፍቃድ ሰበብ ታስረዉ የሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን የድረሱልን ጥሪ መልስ አልባ ሆኖ አይምሯቸዉን እየሳቱ የሚንገላቱ ወገኖቻችን መበራከታቸዉን ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በተለይም የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ኢንባሲ በኒንዴላ በእስር ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን ሊሴ ፓሴ ወይም የምጓጓዣ ወረቀት ለምስጠት ባለመቻሉ እና አፋጣኝ ምላሽ ባለማድረጉ በየወቅቱ ኢትዮጵያዊያን እንደሚሰቃዩ የደቡብ አፍሪካ የስደተኞች ቢሮ ( DEPARTMENT HOME AFFAIRS ) ቅሬታዉን ማሰማቱን ቀጥሏል።
ደቡብ አፍሪካ በከፍተኛ ደረጃ የወያኔ ተቃዋሚዎች የሚንቀሳቀሱበት ሐገር ስትሆን ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ስደተኞችንም በብዛት ተጠልለዉባት ይገኛሉ በዚያ የሚኖሩ ወገኖቻችንን በተቻለን ሁሉወደ ሐገራቸዉ በሰላም ይመልሳቸዉ ዘንድ የወያኔን መንግስት ግበአተ መሬት ያፋጥነዉ ዘንድ ተግተን እንድንሰራ ጥሪያችንን በኢትዮጵያ ስም እናቀርባለን!!
ድል ለኢትይጵያ ህዝብ ! !
ጉድሽ ወያኔ

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: