በደቡብ ክልል ስርዓቱን የሚያወግዙ በራሪ ወረቀቶች ተበተኑ

11329989_1062444910449995_7995307124947863635_n

በደቡብ ኢትዮጵያ በተየያዩ አካባቢዎች ስርዓቱን የሚያወግዙና ለትግል የሚያነሳሱ ወረቀቶች መበተናቸውን ዛሬ ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ። በደቡብ ኢትዮጵያ አዋሳ፣ ሆሳዕና፣ ሳዉላ እና ሶዶ ከተሞች እሁድ ምሽት የበተናቸው ወረቀቶች የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ፎቶ ግራፍ የያዙ ሲሆን፣ የጋራ ትግል ጥሪ መልዕክቶችን እንደሰፈሩበት ተገልጧል።

አርበኞች ግንቦት 7 አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የተለያዩ የጥሪ ወረቀቶች እያሰራጩ መቆየቱ መግለጽ የሚታወቅ ሲሆን፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባለፈ ዕሁድ ዋሽንግተን አቅራቢያ ሲልቨርስፕሪንግ ከተማ በተካሄደ ህዝባዊ ስብሰባ ሃገር ቤትም ድርጅታቸው በጉልህ እንደሚንቀሳቀስ መግለጻቸው ይታወሳል።

ጊዜው ሲደርስ ህዝባዊ ዕምቢተኝነትና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል በቂ አቅም በሃገር ውስጥ እንዳለም ተናግረዋል።

አርበኞች ግንቦት 7 በህዝባዊ ዓመጽና በመሳሪያ ሃይል ስርዓቱን ለመለወጥ የሚንቀሳቀስ ቡድን መሆኑ ይታወቃል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: