የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት በኢትዮጵያ ተጨማሪ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች መኖራቸውን አስታወቀ

ከሰላሳ ዓመት በኋላ የተከሰተውን ዘግናኝ የርሃብ አደጋ ተቋቁሞ የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ ይቻል ዘንድ የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት USAID የ100 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር ተጨማሪ የምግብ እርዳታ ልገሳ አደረገ። ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 10.5 ሚልዮን ኢትዮጵያዊያን መኖራቸውን አመልክቶ ይህ አሃዝ በቅርቡ እንደሚያሻቅብ ስጋቱን ጠቁሟል።
የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት USAID ሃላፊ የሆኑት ጋይሌ ስሚዝ የሁኔታውን አሳሳቢነት ሲገልጹ ”አስከፊው እርሃብ ያስከተለው ቀውስ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል የኢትዮጵያ ሕዝብ የእኛ እርዳታ በአፋጣኝ ያስፈልገዋል”
በተጭማሪም አሉ ጋይሌ ስሚዝ ”በአፋጣኝ ተጨማሪ ግብአቶችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ ገበሬዎቹን ወደ አምራችነት እንዲመለሱ በማድረግ ከዚህ ቀውስ እንዲወጡ ማስቻል አለብን!” በማለት ለረድኤት ድርጅቶችና ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፕሬዝዳንት ባንኪ ሙን በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ በተከሰተውን ድርቅ ሳቢያ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት አስከፊ የምግብ ጥረት ስለሚከሰት ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው በፊት የእርዳታ እጃቸውን በአፋጣኝ እንዲዘረጉ ተማጽኖዋቸውን አቅርበዋል።
ባንኪሙን አክለውም ”አፋጣኝ ልገሳ በማድረግ የብዙዎችን ሕይወት በማዳን ቀውሱን መከላከል አለብን!” ሲሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለበትን አስጊና አስፈሪ የርሃብ አደጋ ጠቁመዋል።
ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በድርቅ የተጠቁ አካባቢዎችን በጎበኙበት ወቅት የተባበሩት መንግስታትና ዓለም አቀፍ ለጋሾች በጋራ 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማለትም ከሃያ ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

posted by Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: