በሄግ ከሚገኘው አለም አቀፍ ፍርድ ቤት አፍሪካዊያን እንዲወጡ ይደረግ ዘንድ መሪዎቹ ተስማሙ

የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ጓደኞቻቸውን ከአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አገሮቻቸውን እንዲያስወጡና ህብረቱም ለዚህ የሚሆን የመውጫ ስትራቴጂ እንዲነድፍ ጠይቀዋል፡፡ህብረቱም የኡሁሩን ፕሮፖዛል ያለምንም ማሻሻያ መቀበሉን አስታውቃቋል፡፡
ፕሬዘዳንት ኡሁሩ አጽንኦት በመስጠትም ለሚኒስትሮች ኮሚቴ ኃላፊነት ተሰጥቶ በሄግ ከሚገኘው አለም አቀፍ ፍርድ ቤት አፍሪካዊያን እንዲወጡ ይደረግ ዘንድ ወትውተዋል፡፡ አለም አቀፉን ፍርድ ቤት ልአላዊነታችንን ለማጥፋት የተዘጋጀ መሳሪያ ነው ያሉት ኡሁሩ‹‹የአፍሪካ ህብረት ለመንግስታት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ያለመከሰስ መብት እንዲያስከብርና ጉዳያቸው በፍርድ ቤቱ እየታየ የሚገኘውን የምክትል ፕሬዘዳንታቸውን ዊልያም ሩቶ ክስ እንዲቋረጥ ጫና እንዲፈጥር ጠይቀዋል››፡፡
የ2007ቱን የኬንያ አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ እጃቸው እንደሚገኝበት የተጠረጠሩት የኡሁሩ ምክትል ሶስት ክሶች ቀርበውባቸዋል፡፡ የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በኡሁሩ ላይ አቅርበውት ለነበረው ክስ ማስረጃና ምስክሮችን ማግኘት ባለመቻላቸው የፕሬዘዳንቱን ክስ እንዲቋረጥ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡ከዊልያም ሩቶ ጋር የተከሰሰው የራዲዩ ጋዜጠኛው ጆሽዋ ሳንግ ጉዳዩን በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡
የሱዳኑ ፕሬዘዳንትና የተወሰኑ ባለስልጣናቶቻቸው በምዕራብ ሱዳን በምትገኘው ዳርፉር ለተፈጸመ ኢሰብአዊ ድርጊት ተጠያቂ በመደረጋቸው ክስ የተመሰረተባቸው ቢሆንም በአዲስ አበባ ተገኝተው አፍሪካ ከፍርድ ቤቱ አባልነት እንድትወጣ በኡሁሩ የቀረበውን ሐሳብ ደግፈዋል፡፡
በ2002 የሮም ስምምነት መጽደቁን ተከትሎ የተመሰረተው አለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በእስካሁን ቆይታው ከ39 በሚልቁ የአገር መሪዎችና የጦር ሹማምንት ላይ ክስ መስርቷል፡፡በወንጀል ፍርድ ቤቱ በአብዛኛው ክስ የተመሰረተባቸው አፍሪካዊያን መሆናቸውም በአህጉሪቱ ባለስልጣናት ፍርድ ቤቱ ጥርስ ተነክሶበት ቆይቷል፡፡
ለሮም ስምምነት ይሁንታቸውን የሰጡ 34 የአፍሪካ አገራት የፍርድ ቤቱ አባላት ናቸው ፡፡ኬንያ ከምስራቅ አፍሪካ አገራት መካከል ለሮም ስምምነት እውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ ብትሆንም አሁን ከአባልነት ለመውጣት ግምባር ቀደም ተዋናይ በመሆን ጥሪ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡
የአፍሪካ አገራት ከአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አባልነት እንዳይወጡ አጥብቀው ሲታገሉ የቆዩት ደቡብ አፍረካዊው ቄስ ዴዝሞንድ ቱቱ ‹‹በፍጹም መውጣት የለባቸውም፡፡መሪዎቹ ይሀንን ለማድረግ የሚፈልጉት ያለ ተጠያቂነት ለመግደል፣ለማሰርና ቶርቸርን ለመፈጸም ነው ፡፡እንደ ዘር ማጥፋት ያሉ ወንጀሎችን ከአፍሪካ ለማስወገድ ፍርድ ቤቱ መኖር ይገባዋል››ብለዋል፡፡
የዴዝሞንድን አስተያየት የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ኮፊ ሃናንም ይጋሩታል፡፡ኮፊ ‹‹ፍርድ ቤቱን የሚታገሉትና ተቃርነው ድምጽ በመስጠት ጉዳያቸውን ከፍርድ ቤቱ ካስሰረዙ ለህብረቱ መሪዎቻችና ለአገሮቻቸው ትልቅ ሐፍረት ነው››ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
በ2006 በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባን በአዲስ አበባ በመገኘት ተካፍለው የነበሩት የፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ፊሊፕ ኪርሴች ‹‹እስከሚገባኝ ድረስ ፍርድ ቤቱ ያለአፍሪካዊያን ድጋፍ መቀጠል አይችልም››ብለው ነበር፡፡
እርስዎ ምን ይላሉ?

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: