“በአኮቦ ወረዳ ከ200 በላይ የሚሆኑ አኙዋኮች ህፃናት እና ሴቶች መጨፍጨፋቸው ተነገረ

ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም

ሁላችንም እንደምንገነዘበው ባለፋት 25 አመታት ወያኔ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ስሌቶችና ጭካኔና በተሞላበት ድርጊቶች መካከል የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር በሀይማኖት እና በክልል እየከፋፈለ አንዱን ብሄረስብ በሌላው ላይ እያነሳሳና እያስታጠቀ ለመቆየት በመቻሉ ነው። በተናጠል ሌላውን ብሄረሰብ እያጠቃ በጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈፅመው የኢሰብዓዊ ድርጊቶች ከማንኛውም ግዜ በላይ በመቀጠል ላይ ነው ያለሁ። ለዘመናት በሰላም እና በፍቅር ይኖር የነበሩትን ብሄረሰቦች እርስ በእርስ በማጋጨት በሌላው ብሔረሰብ ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻም እያወጀና እየጨፈጨፈ ሲያንስም የሕዝቡን ነፃነት እየሸረሸረ ዛሬ በበለጠ ግዜ የሀገሪቷን ሉዓላዊነት አወዛጋቢ ሁኔታ ላይ ጥሎዋታል።

መላው የአለም ህዝብ እንደሚያውቀው ታህሳስ 3፣1996 ዓ.ም (December 13, 2003) በጋምቤላ ከተማና በተለያዩ ወረዳዎች ዉስጥ ከሶስት ሺህ በላይ የሚበልጡ እኙዋኮች እንደ እንስሳ በወያኔ የታደኑበት ቀን ነች። ይህን ድርግት በተመሣሣይ ሁነታ በሌላው የኢትዮጵያ ብሕረሰብ ላይ እንዳይደገምና መላዉ የአለም ሕዝብ ይህን ታርካዊ ቀን እንድያስታውሳትና እንዳይረሱት ምክንያት ተደርጎ ይህንን ድርጅት በዚቹ ቀን እንድሠየም ተደርጓል። አሁንም ቢሆን በአኙዋኮች ላይ በሌላ መልኩ ተመሳሳይ ግድያ እየተካሄደ ነው። ባለፈው ወር ብቻ በአኮቦ ወረዳ ከ200 በላይ የሚሆኑ አኙዋኮች ህፃናት እና ሴቶችን ጭምር ወያኔ ባስጣጠቃቸው ከባድ የጦር መሳሪያዎች በስደተኛው ንዋር ብሄረሰብ ተጨፍጭፈዋል። እንዲሁም አኮቦ ወረዳ አልፎ በተመሳሳይ ሁኔታ ደግሞ በኢታንግ ወረዳ የሚገኙ ቀበሌዎች በነዚህ የጦር መሣርያዎች በመደብደብ በርካታ በቶችና ንብረቶችን ተጋይተው 18 በላይ የሚበልጡ አኙዋኮች መገደላቸው እና በርካቶች መቁሰላቸው ለአለም ተገልፆዓል።

በተጨማሪ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝና የተቀሩት ከፍተኛ የወያኔ ባለሥልጣን በተገኙበት ለውሸት ፕሮፓጋንዳ ተብሎ በጋምቤላ የብሄርና ብሄረስቦች በሚከበርበት ቀን ለአኙዋኮች መግደያ እንዲሆን የታቀደው የጦር መሳሪያ የተከማቸበት ግምጃ ቤት እንዳይከፈት በትህዛዛቸው የተከለከለ ሲሆን ፣ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ እነዚህን መሳሪያዎች ለአጋሩ የንዋሩ ብሕረሰብ ለማከፋፈል ስሞክሩ የጫኑበት መኪና ላይ በኬላ ላይ በመያዙ እስከ ዛሬ ድረስ ማንም በዚሁ ሽብር የተጠየቀ እንዳልነበረ ነው። በአለፋት ቀናት በዜና ምንጮች ስዘገቡ የነበረው የጋምቤላ አሳሳቢ ሁኔታ የንዋሩና የወያኔ ሴራዎች በመሆናቸዉ የአኝዋክ ብሕረሰብ ለዘመናት በዘግነቱ የኮራ ለአገሪቷን ሉዑላዊነት ከሚገባው መጽዋትነት የከፈለ በወያኔ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ያልተበገረ አኩሪ ታሪክ ያለው ሕዝብ ነው። ይህን ሆኖ እያለ ወያኔና ግብረአበሮቹ የአቀዱትን የአኝዋኩ ብሕረሰብ የመጨፍጨፍ ሴራ ማንኛውም ኢትዮጵያዊና የአለም ሕብረተሰብ በጥብቅ እንድያወግዘውና እንድያከሽፍ ያስፈልጋል። በመቀጠልም በአዲስ አበባ አካባቢ የሚገኙ የታወቁ እና ያልታወቁ አስቃቂ እስር ቤቶች ክ200 በላይ የሚሆኑ አኙዋኮችና የመጀንገር ብሄረስብ ሀባላት በታህሳስ 3፣ 1996 ዓ.ም ወያኔ በፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጄል በግድያ ወቅጥ በመትረፋቸው ብቻ ተወንጅለው በእነዚህ እስር ቤቶች በመሰቃየት ላይ ናቸዉ።

ትላንት በአማራው በሱማሌው በኦሮሞው በአኙዋኩ በመጀንገር እና በሌሎችም የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሲፈፀም የነበረው ግድያ፣ አሁንም ደግሞ በአዲስ አበባ ማስተርፕላን ጋር የተያያዘው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ሰበብ በማድረግ የወያኔ አሸባሪ ሰራዊት የኢትዮጵያ ህዝብ ጭካኔ በተሞላበት ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸዉ ናቸው። ከዚህም አልፎ የሀገሪቷን ንብረቶች እየዘረፈ፣ መሬቶችን እየነጠቀ እና ህዝቡን በማፈናቀል ለ25 ዓመታት ሁሉ የዘረጉትን የግድያ ስንስለቶች እንዲቆይ ያደረገው ህዝብን በመከፋፈል መሆኑ እየታወቀ አሁን ኦሮሞ ሕዝብ ለነፃነትና ለእኩልነት የሚያካሆደሁን እንቅስቃሴ የአንድ ብሄረሰብ ትግል ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነትን የተመረኮዘ ትግል እንደሆነ ሊታሰብበት ይገባል ።እስከ ዛሬ ድረስ ወያኔ በሌላውብሄረሰብ ላይ በጠናጥል ሲፈፅማቸው የነበሩትን ግድያዎች በጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እንዳልተፈፀመ ተደርጎ ባለመወሰዱ የወያኔ አረመኔነትን እንድያራዝም አድርገናል። በመሆኑም ይህች አገር ከገባችበት ሰቆቃ ለማላቀቅ የመላው የኢትዮጵያ ብሄረስቦች በአንድነት በዘር በሀይማኖት ሳይከፋፈሉ ሁሉን ያካተተ ውህደት በመፍጠር ወያኔ የሚወገድበትን አንድ አላማ መቀየስ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው። ዛሬ በሁሉም አቅጣጫ ህዝቡ ታፍኖል ለነጌይቱ የሚያዘልቃቸውን የነፃነት ትንፋሽም ታግዷል ። ለዘመናት ኢትዮጵያ እንድትኖር ያበቁትን እነ አፄ ቴውድሮስ አፄ ምንሊክ እና ዘርዓይን እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በከፈሉት መስዋትነት ሲሆን በሀገሬ ውስጥ ባርነትን አንቀበልም ብለውነውሞትንየተጋፈጡት።

ስለዚህ ነፃነት በልመና በነፃ እንደማይጎናፀፍ  በመሆኑ፣ ከሰማይ የሰላምና ነፃነት አምላክ  እሲኪወርድ ድረስ የምንጠብቅ ከሆነ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ትኖራለች የሚል ግምት እንደማይኖር ነው።

በመቀጠል ደግሞ ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተላለፍ የሚንፈልገው፧ ወያኔ የሕዝቡን ደም ደፍቶ በዝርፊያ ያካበታቸውን ሀብቶች ፣ የንግድና የኢኮኖሚ አውታሮች [ትራንስፖርትና መገናኛ ዘርፎች]በዘረፋ የተገኙ በመሆናቸሁ በነፃነትና በሰብአዊነት የሚያምኑ በውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በወያኔና በደጋፊያቸ የንግድና የኢኮኖሚ አውታሮች ላይ ማእቀብ እንድጫንባቸው።

በተለያዩ ሀገሮች በድብቅ ያካበቱ የንግድ ዘርፎች የዉጭ ምንዛሬ ምንጭ በመሆናቸውና በነዚ ሀብት በሚሰበሰበሁ በመጠቀም ሕዝቡን የሚጨፈጭፋበትን የጦር መሣሪያ በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አቅሙን በሚፈቅደው ሁነታ ከነዚህ ዘርፎች ጋር አንዳችም የንግድ ግንኙነቶችን እንዳይኖር እንድቆጠቡ።

መንግስት መንግስትነትን የሚያሰኘው ማሟላት የሚገባቸዉ አላፊነቶችና ድርግቶች በጥቂጡ ለመግለጽ፣ በሕዝቡን መካከል ሰላም እንድሰፍን መጣር፣ በሕብረተሰቡ መካከል የሚፈጠሩ አለመግባቶች በሰላማዊ እንድፈቱና በማድረግ፣ የአንድነት ስመት እንድኖርና የአገርቷን ደህንነትና ድምበር ማስከበር ሲሆን ወያኔ ግን በተቃራኒ ሕዝቡን በዘርና በጎሳ እየከፋፈለ፣ እየገደለና የአገርቷን ንብረቶችን እየዘረፈ፣ መሬቱን ለውጭ አገር እየለገሰ፣ ለሰውነት ለነፃነትና ለዲሞኪራሲ እሉኝታ የሌለው፣በጎሰኝነት በዘረኝነት በብሕረተኝነት አጥብቀው የሚያምኑበት በመሆኑ ይህን ስርኀት መንግሥት ባለመሆኑ በሕዝቡ ደምና አጥንት የነደፋቸው ፀረ ሰው ሕገ ወጥ ሕጎች ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዳያከብራቸው ለጠቅላላው ሕዝብ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

በአንድነት በነፃነትና በእኩልነት በፍትህና በዲሞኪራሲ ላይ የተመሠረተ ስሪኀት እንድቋቋም የሚያስችል በጠቅላላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትብብር ብቻ ነው። በዚሁ በመነሳት ዘረኛዉ የአረመኔ ስብስብ ሊፋለሙት የሚያችላቸውን አንድ ዓላማ በመነሳት፣ የፓለቲካ ድርጅቶች ልዩነቶች በማስወገድ፣ በአገር ስሜት ለአሁኑ አጣዳፊ የአገር ማዳን ጉዳይ በጋራ እንድንወጣ በአስቸኳይ ጥሪያችን ስናስተላልፍ፣ ለብዙ አመታት በተናጠል የተሞከሩ የነፃነት እንቅስቃሴዎች የትም እንዳላደረሱን የሚታሰብ ሲሆን አሁንም ከተለያዩ ድርጅቶች እና ብሄረስቦች መካከል የተጀመረውን የመተባበር መንፈስ በሰፊው እንዲቀጥል እና የጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምኞት በመሆኑ ድርጅታችን በዘር እና በክልል የተገደበ ባለመሆኑ ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ተባብረን ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን።

አንድ ኢትዮጵያ አንድ ህዝብ!

E‐mail: dec13codemo@gmail.com የታህሳስ ሶስት መታሰቢያ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: