የትግራይ ክልል መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱ እየተቀጣጠለ ያለውን የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን ለማዳፈን ነገ ወልቃይት ይገባሉ ተባለ

የትግራይ ክልል መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱ ዛሬ ወይም ነገ ወልቃይት ይገባሉ እየተባለ ነው። በጉብኝታቸው ወቅት በአካባቢው ያሉ የህወሓት አመራሮችን እና በሰፈራ የመጡ የትግራይ ተወላጆችን ያነጋግራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የጉብኝታቸው ዋና አላማ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ያለውን የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን ለማዳፈን የቅስቀሳ እና የማስተባበር ስራ ለመሰራት እንደሆነ ታምኗል።
በተጨማሪም ሰሞኑን የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ከፍተኛ የሆነ ፀረ ወልቃይት ቅስቀሳ እያስተላለፉ ይገኛል። የወልቃይትን የአማራነት ጥያቄ ለመቀልበስ የትግራይ መገናኛ ብዙሃን በርተተው እዬሰሩ ነው። ሰሞኑን የትግራይ ክልል ልዩ ባንድ በአዲረመፅ እና በዳንሻ ከተማ የሙዚቃ ድግስ አዘጋጅቶ ያለ ምንም ውጤት በታዳሚ ድርቅ ተመቶ ተገዜን ተሻግሮ መመለሱን ምንጮቻችን ገልፀዋል።በአሁኑ ሰአት የወልቃይት አማሮች በግድ የተጫነባቸውን የትግራይ ማንነት የሚያስታውሳቸው የትግረኛ ሙዚቃ መስማት ፈፅሞ እንደማይፈልጉ የአካባቢው ተወላጆች በምሬት በመግለፅ ላይ ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በትናንትናው እለት ወደ ጎንደር በመምጣት ላይ በነበሩ ተጨማሪ ኮሚቴዎቻችን ላይ የህወሓት ካድሬዎች ወከባ እና እንግልት እንደ ፈፀሙባቸው መገንዘብ ችለናል። ለወደፊቱ ወከባው እየከፋ እንደሚሄድ የህወሓት እብሪተኞች በድርጊት እና በዛቻ ንግግር በመግለፅ ላይ ናቸው። ስለሆነም መላው አማራ ስለ ወልቃይት የአማራ ማንነት ጠያቂ ኮሚቴዎቻችን የየቀን ውሎ ትኩረት ሰጥቶ በንቃት እንዲከታተል እናሳስባለን።

 አሰግድ ታመነ

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to የትግራይ ክልል መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱ እየተቀጣጠለ ያለውን የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን ለማዳፈን ነገ ወልቃይት ይገባሉ ተባለ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: