ኢትዮጵያዊያን በታንዛኒያ እየታደኑ ነው

የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ያላቸውም ሆኑ የሌላቸው የውጪ አገራት ዜጎች የተሰማሩባቸውን የስራ መስኮች ለታንዛናዊያን በማስረከብ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዋል።
ከዳሬሰላም ቶማሰን ሮውተርስ ፋውንዴሽን የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ይፋ እንዳደረገው ከሆነ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ የታንዛኒያ ባለስልጣናት ዝተዋል ።ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ታንዛኒያ የገቡ ስለመሆናቸው ተነግሯል ።
ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ወደ ደቡብ አፍሪካና አውሮፓ ለሚሻገሩ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ዜጎች ዋነኛ መተላለፊያ ሆና መቆየቷ ይታወቃል።
የታንዛኒያ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ቻርለስ ኪትዋንጋ መንግስታቸው ለየት ያለ ዘመቻ በመጀመር በቤት ለቤት አሰሳ በህገወጥ መንገድ ወደ አገር የገቡትንና በስራ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያንንና የውጪ አገራት ዜጎችን በማሰር ለፍርድ እንደሚያቀርቧቸው ገልጸዋል ።
ባለፈው ወር የታንዛኒያ ፖሊስ በደላሎቻቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚሻገሩ ተስፋ ተገብቶላቸው ዳሬሰላም ውስጥ በሚገኝ አንድ ቤት ውስጥ በተፋፈገ ሁኔታ እንዲቀመጡ የተደረጉ 40 ኢትዮጵያውያንን መያዙ ይታወሳል ።
“በህገወጥ መንገድ በአገራችን የሚኖሩ ብዛት ያላቸው የውጪ ዜጎች እንዳሉ እናውቃለን ።እነርሱን በማሰር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ከማድረግ አናመነታም “በማለት የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ መናገራቸው ተሰምቷል ።
ብዙ ሺህ ማይልሶችን በእቃ መጫኛ መኪኖች ህይወታቸውን ለአደጋ በመስጠት ታንዛኒያ የደረሱ ኢትዮጵያውያን በዜናው ከፍተኛ ድንጋጤ ተሰምቷቸዋል ።በ2004 በዳሬሰላም 45 ኢትዮጵያውያን ኮንቴይነር ውስጥ ታሽገው በመኪና ሲጓጓዙ አየር አጥተው ለሞት መዳረጋቸው አይዘነጋም ።
እንደ መንግስት ሪፖርት ከሆነም ስደተኞች በአብዛኛው ከ1000 እስከ 2000 ዶላር ከታንዛኒያ ደቡብ አፍሪካ ለመድረስ ለአዘዋዋሪዎች ይከፍላሉ ።
አዘዋዋሪዎቹ በታንዛኒያ ፣ማላዊና ኬንያ ደህንነታቸው የተጠበቁ ቤቶች አሏቸው የሚለው መንግስት ጠንካራ የሆነ የግኑኝነት ሰንሰለት ደላሎቹ መዘርጋታቸውንም ይናገራል ።
የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ አዲስ አበባ ገብተዋል ።የህብረቱ አገራት መሪዎች ማጉፉሊን በሰሞነኛው ውሳኔያቸው ዙሪያ ያናግራቸው ይሆን ?
የኢህአዴግ መሪዎችስ በታንዛኒያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደህንነት ዙሪያ ስጋት ገብቶናል የማለት ሞራል ያገኙ ይሆን ?

Dawit Solomon Yemesgen's photo.
posted by Aseged Tamene
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: