በቢጫ ወባ መሰል ቫይረስ የተነሳ ሴቶች እንዳያረግዙ እየተመከሩ ነው

ባሳልፍነው ሰኞ አለም አቀፉ የጤና ድርጅት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው ወባ ወለድ ቫይረስ በአሜሪካና በላቲን አሜሪካ በከፍተኛ ደረጃ ሊዛመት ይችላል ብሏል ።
ከግንቦት ወር 2007 ጀምሮ ወደ 21 አገራት መዛመቱ የተነገረለት ቫይረሱ በእርግዝና ወቅት በወባዋ የተነከሱ ወይም ቫይረሱ የያዛቸው ወላዶች ከተለመደው መጠን አነስ ያለ ጭንቅላት ያለውን ህፃን እንደሚወልዱ ድርጅቱ ጠቅሷል ።
አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው ከሆነም በብራዚል ብቻ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል ።በመጪው ክረምት የኦሎምፒክ ውድድሮችን የምታስተናግደው ሪዮ ዲ ጃኔሮ ቫይረሱ እንዳይዛመትባት የየቀን ክትትል ስር ትገኛለች ብሏል ጋዜጣው።
የደቡብ አሜሪካን አገራት መንግሥታት ኮሎምቢያንና ብራዚልን ጨምሮ ሴቶች እርግዝናን እንዲከላከሉ ጠይቀዋል ።ሳልቫዶር በበኩሏ እስከ 2010 የአገሯ ሴቶች እንዳያረግዙ አዛለች።
የ22 ዐመቷ ሳልቫዶራዊት ሳንድራ ባሪኦስ “ይህ የሚቀጥል ከሆነ የቀዶ ጥገና ለማድረግ ባለቤቴን አናግረዋለሁ” ማለቷን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል ።
በአፍሪካና እስያ ከረዥም አመታት በፊት ተከስቶ የነበረው ቫይረሱ እንደ ቢጫ ወባ ስለመሆኑ ተነግሮለታል ።
ትኩሳት ፣የመገጣጠሚያ ላይና ኃይለኛ የራስ ህመም ዋነኛ ምልክቶቹ ናቸው ።በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው የአየር ፀባይ ለውጥ በአንዳንድ አገሮች ያልተጠበቀ ዝናብ ፣ ጎርፍና ወበቅ የሚፈጥር በመሆኑ የወባ በሽታ እንዲስፋፋ መንስኤ ይሆናል ።

Dawit Solomon Yemesgen's photo.
Dawit Solomon Yemesgen's photo.
 Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to በቢጫ ወባ መሰል ቫይረስ የተነሳ ሴቶች እንዳያረግዙ እየተመከሩ ነው

  1. Pingback: በቢጫ ወባ መሰል ቫይረስ የተነሳ ሴቶች እንዳያረግዙ እየተመከሩ ነው - EthioExplorer.com

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: