በኢትዮጵያ የታሰሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ‹‹ራሳቸውን እንዳያጠፉ›› ተሰግቷል

በኢትዮጵያ ወህኒ ቤት የሚገኙት እንግሊዛዊ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ሪፕራይቭ ኢንተርናሽናል የሰብዓዊ መብት ድርጅት የጠየቀው የእስረኛውን የአእምሮ ጤንነት በተመለከተ በሳይካትሪስቶች የቀረበው ሰሞነኛ ሪፖርት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አስቸኳይ ህክምና ማግኘት እንደሚገባቸው በመምከሩ ነው ብሏል ዴይሊ ሜይል ጋዜጣ፡፡
በ2014 ከየመን አውሮፕላን ማረፊያ ታፍነው ወደ ኢትዮጵያ የተወሰዱት አቶ አንዳርጋቸው እስካሁን በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡በ1970ዎቹ መጀመሪያ በስደት ከኢትዮጵያ የወጡት የሶስት ልጆች አባት የሆኑት አንዳርጋቸው በ1979 በእንግሊዝ የፖለቲካ ጥገኝነት በማግኘት በሂደት ዜግነት ተሰጥቷቸዋል፡፡
በ2009 መንግስትን በሃይል ለመገልበጥ አሲረዋል ተብለው በሌሉበት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ቢሆንም በክሱ የቀረበባቸውን ውንጀላ አንዳርጋቸው ሲያስተባብሉ ቆይተዋል፡፡
የሳይካትሪስቶቹ ጥናት የእንግሊዝ አምባሳደር በኢትዮጵያ አንዳርጋቸውን በመጎብኘታቸውና የአንደርጋቸው ባለቤት ወይዘሮ ያሚ ሃይለማርያም ከሰጧቸው መረጃዎች በመነሳት የተሰራ ስለመሆኑም ተነግሯል፡፡ሳይካትሪሰቶቹ በድምዳሜያቸውም አንዳርጋቸውን አሁን ከሚገኙበት ሁኔታ ማስወጣት ‹‹በጣም በአስቸኳይ›› መፈጸም እንደሚገባው መክረዋል፡:፡
ፍጹም ንጽህና በጎደለው አነስተኛ ክፍል ዶክተርና ጠበቃ እንዳያገኙ ተደርገው የታሰሩት አንዳርጋቸው ራሳቸውን እንዳያጠፉ መሰጋቱንም ጋዜጣው አስነብቧል፡፡
የእንግሊዙ ኤን ኤች ኤስ ትረስት ኃላፊ ዶክተር ቤንጃሚን ሮቢንሰን ሪፕራይቭ የተሰኘው አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅት የአንዳርጋቸውን የአእምሮ ጤንነት የተመለከተውን ሪፖርት ያወጣው በአንዳርጋቸው ፈቃድ መሆኑን በመግለጽ ‹‹የደረሳበቸው ችግር በቀላሉ የማይስተካከል ነው›› ብለዋል፡፡
ዶክተሩ ‹‹ከወህኒ ቤት እንደተለቀቁም የስነ አእምሮ ጤንነታቸው እንዲያገግም ለማድረግ ረዥሙን ስራ መስራት ይጀመራል፣ ልምድ ባካበቱ ቴራፒስቶችም ተከታታይ የሆነ የሳይኮቴራፒ ህክምናን ለአእምሮ ጤንነታቸው ችግር ተጨማሪ እንክብካቤዎች እንዳስፈላጊነቱ እየተደረላቸው መከታተል ይጀምራሉ››በማለት ጽፈዋል፡፡
‹‹ያ እስኪሆን ድረስ ግን ሁኔታዎቹ እየከፉ በመሄድ ራሳቸውን ሊያጠፋ ይችላሉ የሚለው የበለጠ አሳሳቢ ይሆናል፡፡ በህይወት መቆየት ቢችሉ እንኳን አእምሯቸው ላይ የሚደርሰው ጉዳት ፈጽሞ የማይጠገን ይሆናል››በማለትም ስጋታቸውን አስፍረዋል፡፡
ዶክተሩ አክለውም የሚጠቅሱት አዲሱ ሪፖርት የአንዳርጋቸው የአእምሮ ጤንነት ማሽቆልቆል የጀመረው በኢትዮጵያ ከታሰሩበት ዕለት አንስቶ መሆኑን እንደሚገልጽ ተናግረዋል፡፡
ሪፕራይቭ ኢንተርናሽናል በበኩሉ የእንግሊዝ መንግስት አንዳርጋቸውን ከኢትዮጵያ ወህኒ ቤት እንዲያስለቅቅ ጠይቋል፡፡
የእንግሊዝ መንግስት የውጪ ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ በ19 የተለያዩ የሁለቱ መንግስታት ግኑኝነቶች ኢትዮጵያን አንዳርጋቸውን በተመለከተ መጠየቁን ገልጸዋል፡፡
የቢሮው ቃል አቀባይ አንዳርጋቸው ህጋዊ ከለላ ማግኘት እንደሚገባቸው መንግስታቸው መጠየቁንም አስረድተዋል‹‹የእንግሊዝ መንግስት ጣልቃ መግባቱን ተከትሎ አንዳርጋቸውን መጎብኘት መቻሉን እንደመልካም ነገር እንቀበለዋለን፡፡ነገር ግን የበለጠ መደበኛ እንዲሆንና ጠበቃ የማግኘት መብታቸውም እንዲከበር እንፈልጋለን››ብለዋል፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to በኢትዮጵያ የታሰሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ‹‹ራሳቸውን እንዳያጠፉ›› ተሰግቷል

  1. Pingback: በኢትዮጵያ የታሰሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ‹‹ራሳቸውን እንዳያጠፉ›› ተሰግቷል - EthioExplorer.com

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: