62 ቱጃሮች የአለማችንን ግማሽ ሀብት ማካበታቸውን ተናገረ፡፡

ኦክስፋም ባወጣው አዲስ ሪፖርት በቁጥር ከ62 የማይበልጡ ቱጃር ግለሰቦች ከአለም ህዝብ ግማሹ ይኖረዋል ተብሎ የሚገመተውን ሀብት የሚስተካከል ነዋይ ማካበታቸውን ተናገረ፡፡ 3.5 ቢሊዮን የሚጠጉ የአለም ህዝቦች ያላቸው ሀብት ቢደመር ከነዚህ 62 ቱጃሮች ሀብት ጋር እኩል ነው የሚለው ድርጅቱ ከነዚህ ቱጃሮች ደግሞ ገሚሶቹን ምትይዘው አሜሪካ መሆኗን ነው የተናገረው፡፡

ኦክስፋም በአዲሱ ሪፖርት ይፋ ካደረጋቸው ሌሎች አስደንጋጭ እውነታዎች መካከል የአለም ጥቂት ቱጃር ግለሰቦች መጠኑ 7.6 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብትን ከታክስ አሽሽተው በድብቅ እንደሚያስቀምጡ እንደተደረሰበት የሚገልፀውም ይገኝበታል፡፡ ድርጅቱ እንደሚለው ይህ ሁሉ ቁልል ሀብት ወደ ታክስ ስርዓት እንዲገባ ቢደረግ ለአለም መንግስታት እስከ 190 ቢሊዮን ዶላር የታክስ ገቢ ይፈጥራል ተብሏል፡፡

አህጉራችን አፍሪካ ገንዘብ በየዓመቱ እየኮበለለ በህገወጥ መንገድ እንደሚሰደድባት የሚጠቅሰው ኦክስፋም አህጉሪቱ እስከ 30 በመቶ የሚሆነው ገንዘቧ በታክስ ሽሽት እንዲወጣ እንደሚደረግ ተናግሯል፡፡ ይህ አህጉሪቱን ይበልጥ እንድትደኸይ እንደሚያደርግ የሚገልጸው ተቋሙ አፍሪካ በየዓመቱ በዚህ ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰት እስከ 14 ቢሊዮን ዶላር ታጣለች ብሏል፡፡ ይህ የህገወጥ ገንዘብ ስወራ መጠን አህጉሪቱ በጤና አገልግሎት እጦት በየዓመቱ የአራት ሚሊዮን ህጻናቶቿ ህይወት እንዳይቀጠፍ ለማድረግና ለመላው አህጉሪቱ ህጻናት ትምህርት ለማዳረስ የሚበቃ ነው ይላል፡፡

እነዚህ ቀሪው አለም ሲደኸይ እነርሱ ይበልጥ በሀብት እየከበሩ የሚሄዱ ቱጃሮች ናቸው እንግዲህ ሰሞኑን በስዊዘርላንድ ዳቮስ ተሰባስበው ስለአለማችን ድህነት ቅነሳ እየመከሩ የሚገኙት፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to 62 ቱጃሮች የአለማችንን ግማሽ ሀብት ማካበታቸውን ተናገረ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: