የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ከህገ-ወጥ ተግባሩ እንዲታቀብ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው

“ኮረም ሳይሞላ የተወሰነ ውሳኔ ስለሆነ ህገ ወጥነቱን ተቃውመናል” ኢ/ር ይልቃል

የሰማያዊ ፓርቲ ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን፤ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከሥልጣኑ ውጭ በመሄድ ከሚፈጽመው ህገ-ወጥ ተግባር እንዲታቀብ አስጠነቀቀ፡፡ “የፓርቲው የስነ-ስርዓት ኮሚቴ በምክር ቤት አባላቱ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ኮረም ያልተሟላበት ስለሆነ የስራ አስፈፃሚው ህገወጥነቱን ተቃውሟል” ብለዋል – የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፡፡
የሰማያዊ ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ትላንት ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፤ ከጠቅላላ ጉባኤው ቀጥሎ ከፍተኛ ስልጣን ያለው ብሄራዊ ምክር ቤቱ፤ ከፓርቲው ህግና ደንብ ውጭ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከፋፋይና በህዝቡ መካከል ጥላቻን የሚፈጥር ፅሁፍ አሰራጭተዋል ባላቸው 4 አባላት ላይ ክስ መስርቶ፣ የስነ ሥርዓት ኮሚቴው ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ አባላቱ እንዲባረሩ መወሰኑን አስታውሶ፤ ሥራ አስፈፃሚው ከተሰጠው ስልጣን ውጭ  ውሳኔውን አልቀበልም ማለቱ ህገወጥነት ነው ብሏል፡፡
ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽኑ፤ አንደኛው ተሰናባች አቶ ዮናታን ተስፋዬ አሁን ባለበት ሁኔታ ራሱን መከላከልም ሆነ ይግባኝ መጠየቅ ስለማይችል በሱ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያየት የጠየቅናቸው የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው፤ “ስራ አስፈፃሚው፤ ችግር ሲፈጠር ለኦዲትና ምርመራ ኮሚሽኑ ይግባኝ አይባልም ወይም የስነ-ስርዓት ኮሚቴው የመወሰን መብት የለውም አላለም፤ ውሳኔው መተላለፍ ያለበት የስነ-ስርዓት ኮሚቴው ምዕላተ ድምፅ ሲሞላ ነው፤ ሆኖም ባልተሟላ ድምፅ ውሳኔው በመተላለፉ ህገወጥነቱን ተቃውመናል” ብለዋል፡፡ በፓርቲው ህግና ደንብ መሰረት ውሳኔ ለማስተላለፍ ምዕላተ ድምፁ 50 + 1 መሆን እንዳለበት ያብራሩት ኢ/ሩ፤ በምክር ቤት አባላቱ ላይ ውሳኔ ያስተላለፉት ከሰባቱ የስነ-ሥርዓት ኮሚቴ አባላት ሶስቱ ብቻ እንደነበሩና አንደኛው አባል በሂደቱም በፊርማውም እንዳልተሳተፈ ምስክርነቱን ሰጥቷል ይላሉ፡፡ “እኛ ተቃውሞ ያነሳነው ውሳኔ ባገኘ ጉዳይ ላይ እንጂ ገና በእንጥልጥል ላይ ባለ ጉዳይ ባለመሆኑ ህጉን ተከትለን እየሰራን ለመሆናችንን ማሳያ ነው” ሲሉም ኢ/ር ይልቃል – ተሟግተዋል፡፡ የፓርቲው የስነ-ስርዓት ኮሚቴው በአባላቱ ላይ ውሳኔ ሲያስተላልፍ ኮረም መሙላት አለመሙላቱን በተመለከተ የጠየቅናቸው የኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ሀና ዋለልኝ፤ በውሳኔው ላይ ከሰባቱ የኮሚቴ አባላት አራቱ መገኘታቸውንና አራቱም በውሳኔው መስማማታቸውን ገልፀው፣ ውሳኔው ከተላለፈ በኋላ ሲሳይ ካሴ የተባሉት አባል ከውሳኔው ማፈንገጣቸውን እንዲሁም ውሳኔውን መካዳቸውን ጠቁመዋል፡፡ “ያም ሆነ ይህ ውሳኔው ሲተላለፍ ከሰባት አባላት አራቱ መገኘታቸው ኮረም እንደሞላ ያሳያል” ያሉት ሰብሳቢዋ፤ አቶ ሲሳይ ካሴ ውሳኔውን ቢክዱም ሶስታችን በመስማማታችን ኮረም አልሞላም መባሉ አግባብ አይደለም ሲሉ አስተባብለዋል፡፡ addisadmas

posted by Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ከህገ-ወጥ ተግባሩ እንዲታቀብ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: