በጥቁር አንበሣ ወጣቱ የምጥ መርፌ ተወግቶ ሲያምጥ አደረ

ወጣት ካሊድ ባደረበት ድንገተኛ ህመም በቤተሰቦቹ ተደግፎ በአቅራቢያው ጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ያቀናል። አስፈላጊውን ምርመራ ካደረገ በኃላም መድሃኒትና መርፌ እንደታዘዘለት ቤተሰቦቹ ይገልጻሉ። ካሊድ መኖሪያ ቤቱ እንደደረሰ አዲስና ከበፊቱ የተለየ የህመም ስሜት እንደ ጀመረው የሚገልጹት ወላጆቹ «ከሆስፒታል መልስ ሌሊቱን በከባድ ምጥ ሲሰቃይ ማደሩን ይናገራሉ » ።
የሰውነቱ በላብ መጠመቀና ፤ ማማጥ ግራ የተጋቡ ወላጆች በምጥ የሚሰቃየውን ወጣት ተሸክመው ዳገም ወደ ሆስፒታሉ ይመለሳሉ።
በወቅቱ ለካሊድ እርዳታ ሲያደርጉለት የነበሩት ሃኪም የስራ ሰዓታቸውን ጨርሰው በመውጣታቸው ፣ ዶ/ሩን ተክተው የሚሰሩ ተረኛው የህክምና ባለሙያ የምርመራውን ፋይል ሲያገላብጡ ለአይን የማይታመንእንግዳ ነገር ይገጥማቸዋል። ከፋይሉ ጋር አባሪ የሆነ ነጻ ህክምና የሚከታተሉ « የአንዲት ነፍሰ ጡር እናት የምርመራ ውጤት » ያገኛሉ። በአንጻሩ ለካሊድ የታዘዘለትን የብርድ መርፌና ኪኒን እንድ ትወስድ የተደረገቸው ነፍሰጡር እናት ያለችበትን ሁኔታ ለጊዜው ማረጋገጥ ባይቻልም ወጣት ካሊድ ግን በአሁኑ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ ባይሳካም መረጃውን ላደረሱን ወገኖች ደህንነት ሲባል ተጨማሪ መረጃዎችን ከመስጠት ተቆጥበናል። አዲስ አበባ የሚገኘው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ በህክምና ስህተት በዜጎቻችን ላይ በሚፈጸመው ወንጀል ገሚሱ አካለ ስንኩል ሲሆኑ ታክሜ እድናለሁ በሎ ተስፋ ሰንቆ በዋናው በር ወደ ሆስፒታሉ በቁም የሚገባ ዜጋ በሬሳ ሳጥን ታሽጎ በጓሮ በር ሲሽኝ ማየትና መስማት የተለመደ ነው ።
Ethiopian Hagere Jed Bewadi

Dawit Solomon Yemesgen's photo.
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: