የተባበሩት መንግስታት ሶሪያና ኢትዮጵያን በአንድ ምድብ አስቀምጧል

በሁለቱ አገራት ያለው ሁኔታ ለህፃናት አስፈሪ ሆኗል
=====================
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ የቅርብ ዓመታት ታሪክ ውስጥ እጅግ ከፍተኛው በመሆን የተመዘገበው ድርቅ 400.000 ህፃናትን ለአልሚ ምግብ እጦትና 10 ሚልዩን የሚደርሱ ሰዎችን ለምግብ እርዳታ ፈላጊነት ዳርጓቸዋል ብሏል ።
ድርጅቱ በሶስት አስርት ዓመታት ታሪኳ አስከፊው ድርቅ በመሆን የተመዘገበባት ኢትዮጵያ መጥፎውን ጊዜ እንድትቋቋም የ50 ሚልዮን ዶላር እርዳታ ከለጋሾች ጠይቄላታለሁ ማለቱን አልጀዚራ ዘግቧል ።
ሴቭ ዘ ችልድረን በመግለጫው በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ልክ በሶሪያ ያለው ጦርነት ለህፃናት ህይወት አስጊ እንደሆነው በአገሪቱ ለሚገኙ ህፃናትም ድርቁ በአስጊነቱ በተመሳሳይ ደረጃ የሚገለጽ ነው ብሏል ።
የህፃናት አድን ድርጅቱ ተወካይ ካሮሊን ሚልስ “በአለም ላይ ያሉን የአስቸኳይጊዜ እርዳታ ፈላጊዎች ምድብ ሁለት ናቸው ።ሶሪያ አንደኛዋ ስትሆን ኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ናት።ለአስቸኳዩ ችግር መፍቻ 100 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ብለናል “ማለታቸው ተሰምቷል ።
አልጀዚራ በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ድርቅ ያናገረው የአስር ልጆች አባት ሙሐመድ ዱባለ ከድርቁ በፊት 53 ላሞች እንደነበሩት በማስታወስ አሁን የቀሩት አምስት ብቻ መሆናቸውን ይገልጻል ።
ሙሐመድ ለሁለት ጊዜያት ከመንግስት የምግብ እርዳታ ቢያገኝም ከድርቁ ስፋት የተነሳ በቂ አለመሆኑን ይናገራል ።
ሙሐመድ “ለህዝቡና ለልጆቻችን በጣም ሰግቻለሁ ምክንያቱም ዝናብ የለም ።ዝናብ ከሌለ ደግሞ ምግብ ና ወተት ስለማይኖር ሰዎች ይሞታሉ “ብሏል።

Dawit Solomon Yemesgen's photo.Dawit Solomon Yemesgen's photo.
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to የተባበሩት መንግስታት ሶሪያና ኢትዮጵያን በአንድ ምድብ አስቀምጧል

  1. Pingback: የተባበሩት መንግስታት ሶሪያና ኢትዮጵያን በአንድ ምድብ አስቀምጧል - EthioExplorer.com

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: