ጎንደር በብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት ተወራለች

የቤተ አማራ የውስጥ አዋቂዎች እንደገለፁት ሰሞኑን የብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጎንደር ላይ ከትመው ሰንበታዋል። ከብአዴን ወጣት አባላት፣ ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች እና በከተማው ውስጥ ተሰሚነት አላቸው ከሚባሉ ግለሰቦች ጋር የተለያዩ ዝግ ስብሰባዎችን እያካሄዱ ነው። የስብሰባው ዋና አጀንዳ ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ የህዝብ አመፅ በጎንደር ከተማ ውስጥ እንዳይቀሰቀስ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ነው ተብሏል።

የወልቃይት የአማራነት ጥያቄ፣ ለሱዳን ሊሰጥ የታቀደው ሰፊ እና ለም የአማራ መሬት፣ ከቅማንት ማህበረሰብ የአስተዳደር ይገባኛል ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተነሳው ደም ያፋሰሰ ግጭት፣ በአጠቃላይ በግልፅ እዬታዬ ያለው ከፍተኛ የሆነ የአማራ ህዝብ በደል የጎንደር እና የአካባቢውን ኗሪዎች በጥምቀት እለት ወደ ህዝባዊ አመፅ እናዳያመሩ በብአዴኖች ላይ ከፍተኛ ፍርሃት አሳድሯል። የጎንደር ጥምቀት በዓል በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በየአመቱ እንደሚያከብረው ይታወቃል።

ብአዴኖች ከፍርሀታቸው የተነሳ በተለይ ጥር 12 የሚከበረውን የቅዱስ ሚካኤልን ንገሰ በዓል ለመሰረዝ የታሰበ እቅድ አቅርበው ነበርም ተብሏል። ከጥር አስራ አንዱ የጥምቀት በዓል በኋላ በማግስቱ የሚከበረው ይሄው በዓል እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ ለዘመናት ሲከበር እንደኖረ የሚታወቅ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ የህዝብ ብሶቶች በተለይ በቅዱስ ሚካኤል ታቦት የማስገባት ቀን ሲንፀባረቁ ተስተውሏል። የብአዴን ፍራቻ የመጣውም ከዚህ ጋር ተያይዞ መሆኑ ታውቋል። ይሄን የብአዴን ሃሳብ ተስብሳቢው መሉ ለሙሉ በምሬት ውድቅ እንዳደረገባቸው ምንጮቻችን አያይዘው ገልጸዋል።

ሌላው ለብአዴን የጎን ውጋት የሆነበት ችግር እሱ ባላሰበው መልኩ ከቁጥጥሩ ውጭ እየወጣ ያለ ጠንካራ የአማራ ብሔርተኝነት እየተቀጣጠለ መሆኑ ነው። ብአዴን በሕወሓት የሚመራ የይስሙላ ብሔርተኝነት እንጂ እንዲህ አይነቱን የአማራ ብሔርተኝነት እንደማይፈልገው በተዘዋዋሪ ለተሰብሳቢው ሲገልፅ ተደምጧል።

ብአዴን በተደጋጋሚ የአማራን ህዝበ ጥቅም ማስጠበቅ ሳይችል የቀረ ደካማ ፓርቲ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ሁለት አስርተ አመታት ተቆጥሩ።

ድል ለአማራ ህዝብ!

posted by Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: