የታንዛኒያ ፖሊስ የ83 ኢትዮጵያውያንን ህይወት አተረፈ
January 18, 2016 1 Comment
የታንዛኒያ ፖሊስ ወደ ደቡብ አፍሪካ እያመሩ የነበሩ 83 ኢትዮጵያውያንን መያዙን የአገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል ።
ስደተኞቹ በዕቃ መጫኛ መኪና አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ ተደራርበውና እጅግ በተፋፈነ ሁኔታ እየተጓዙ በታንዛኒያና ማላዊ ድንበር አቅራቢያ መያዛቸውን የገለፀው ፖሊስ ብዙዎቹ ጥቂት ዘግይተን ቢሆን ኖሩ ህይወት አናገኛቸውም ነበር ማለቱን የታንዛኒያ ሲቲዝን ጋዜጣ ዘግቧል ።
የፖሊስ ኃላፊው ካካምባ “በጣም ተዳክመውና ተጠምተው ነበር ።በመኪናው ውስጥ ተደራርበው እንዲቀመጡ ተደርገዋል ።ነርሶችን በመያዝ እርዳታ እንዲያገኙ አድርገናል”ብለዋል።
ጥቂት ደቂቃዎችን ብንዘገይ በህይወት አናገኛቸውም ነበር የሚሉት ካካምባ “በመጥፎ ደረጃ ላይ ነበሩ ።በተፋፋነ ሁኔታ ውስጥ ስለነበሩም ይሞቱ ነበር “ይላሉ ።
ባለፈው ዓመት 100 ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያመሩ ታንዛኒያ ውስጥ መያዛቸው አይዘነጋም ።
በ2012 በዕቃ መጫኛ መኪና ተሸፍነው ይጓዙ የነበሩ 40 ኢትዮጵያውያን በመሀል ታንዛኒያ ሞተው መገኘታቸው ይታወሳል ።

Pingback: የታንዛኒያ ፖሊስ የ83 ኢትዮጵያውያንን ህይወት አተረፈ - EthioExplorer.com