አልሻባብ በሶማሊያ 63 የኬንያ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ

የኬንያው ፕሬዘዳንት ዛሬ ባደረጉት ንግግር አልሻባብ በሶማሊያ የሚገኘውን የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ጦር ካምፕ በማጥቃቱ ኬንያዊያን ወታደሮች መገደላቸውን ገልጸዋል፡፡ፕሬዘዳንቱ ምን ያህል ወታደሮች በጥቃቱ እንደተገደሉ ባይገልጹም የአልሻባብ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል 63 የኬንያ ወታደሮች መገደላቸውን ጠቅሷል፡፡
ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሁኔታው በጣም አሳዛኝ እንደነበር በማብራራት ‹‹የተወሰኑት ጀግኖቻችን ዩኒፎርማቸውን እንደለበሱ ትልቁን መስዋዕትነት መክፈላቸውን ስገልጽ ሀዘን ይሰማኛል፡፡ይህንን አጋጣሚ በመጠቀምም የእኔንና የአገሬን ጥልቅ ሐዘን በጥቃቱ ላጣናቸው ወታደሮቻችን ቤተሰቦችና ወዳጆቻቸው ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ከጎናችሁ ነኝ፣ኬንያም በዚህ ወቅት ከእናንተ ጋር ትቆማለች››ብለዋል፡፡
አልሻባብ የአፍሪካ ህብረትን የሰላም አስከባሪ ጦር ካምፕ በመደብደብ ጥቃት ያደረሰው በሶማሊያ ደቡባዊ ክፍል ኤል አዴ ከተማ ነው፡፡ቡድኑ ካምፑን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠሩን ከመግለጹም በላይ የአይን እማኞች በካምፑ ላይ የአልሻባብ ባንዲራ ተውለብልቦ ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡
ቁጥራቸው ያልተገለጸ የኬንያ ወታደሮች አስከሬን በከተማው ሲጎተት መዋሉም ተዘግቧል፡፡ የኬንያ ጦር ቃል አቀባይ በሰጡት ቃል ጦራቸው በድጋሚ በማጥቃት ካምፑን መልሶ በእጁ አስገብቷል ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ኮሎኔል ዴቪድ ኦቦኖዮ ለቢቢሲ የተገደሉባቸውን ወታደሮች ብዛት በቁጥር ባያስቀምጡም አልሻባብ 63 ወታደሮችን ገድያለሁ ማለቱን የተለመደ ፕሮፓጋንዳ ብለውታል፡፡ ኬንያ በሶማሊያ ከሚገኘው 22.000 የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር ውስጥ 4000 ወታደሮችን በማበርከት ከፍተኛውን ቁጥር ይዛለች፡፡
ባለፈው ዓመት ብሩንዲያዊያንና ዩጋንዳዊያን የሰላም አስከባሪ ጦር አባላት በአልሻባብ ታጣቂዎች መገደላቸው አይዘነጋም፡፡

*በሶማሊያ የዶላር ምንጭ እየሆነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ወታደር ምን እየደረሰበት እንደሚገኝ በተባራሪ ከምንሰማው ውጪ እንዲህ ህዝባቸውን አክብረው መረጃ የሚሰጡ የመንግስት ሀላፊዎች የሉንም ለማለት አሰብኩና ለካ በኢትዩጵያ የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የኢትዮጵያ የሚባል ወታደርም የለንም፡፡

Dawit Solomon Yemesgen's photo.
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to አልሻባብ በሶማሊያ 63 የኬንያ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ

  1. Pingback: አልሻባብ በሶማሊያ 63 የኬንያ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ - EthioExplorer.com

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: