በኦሮሚያ አንዳንድ ከተሞች መንግስት ላይ ተቃዉሞዉ ቀጥሏል

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ኪቶ ፋርዲሳ የቴክኖጂ ኢኒስቲቱት ተማሪዎች ትላንት እሁድ ማታ በሰልፍ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የታሰሩ ኦሮሞዎች እንዲፈቱ ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅት ሰባት መኪና ሙሉ የፌዴራል ሃይል ግቢዉ ዉስጥ በመግባት እንደደበደባቸዉ ማንነቱ እንዳይገለጽ የጠየቀ ተማሪ ለአፋን ኦሮሞ ዝግጅግት ክፍል ገልጿል።

ተማሪዎች ድብደባዉን ሸሽተዉ ወደ መኝታ ክፍሎቻቸዉ ሲሸሹበሮችን ሰበርዉ በመግባት በተለይም ኦሮሞዎችን ከሌሎች ተማሪዎች ለይተዉ እንደደበደቡ ተናግሮአል። ይህ በቋንቋ ለይቶመደብደብ ከኦሮሚያ ፖሊሶች በፌደራሎቹ ላይ ጥያቄማስነሳቱንም ተማሪዉ ለአፋን ኦሮሞ ባልደረቦች ገልጿል። በዚሁየኪቶ ፋርዲሳ የቴክኖጂ ኢንስቲቱት በተማሪዎች ላይ በተወረወረቦምብ 7  ተማሪዎች በጽኑ ቆስለዉ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታልህክምና እየተደረገላቸዉ መሆኑ ታዉቋል። ቦምቡን ማንእንደወረወረዉ እስካሁን የተገለጠ የለም። የጂማ ዩኒቨርሲቲፕሬዚደንት ዶክተር ፍቅሬ ስሜን ሰለሁኔታዉ ለመጠየቅ በእጅስልካቸዉ ሳይቀር ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሃሮማያ በሶስት የዩኒቨርሲቲ ካምፓሶችማለትም በቴክኖሎጂ በእርሻና በእንስሰት ህክምና ትምህርትተቋማት እንዲሁም በሃሮማያ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ መሰናዶትምህርት ቤቶች ማስተር ፕላኑ ላይ የሚደረገዉ ተቃዉሞናየታሰሩ ኦሮሞች የፈቱ የሚለዉ ጥያቄ መቀጠሉን የቪኦኤኦሮሚኛ ቋንቋ ክፍል ባለደረቦች ያነጋገሩዋቸዉ ተማሪዎችናየአካቢዉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በሃሮማያ 3  ካምፓሶች በቴክኖሎጂ በእርሻና በእስስሳት ህክምናየትምህርት ተቋማት ዉስጥ ትናንት ማምሻዉ ላይ ” የታሰሩተማሪዎት ይፈቱ እነርሱ እስር ቤት እየተሰቃዩ ፈተና እንፈተንም”እና የመሳሰሉትን መፈክሮች በማሰማት ተቃዉሞ ያደረጉተማሪዎች ላይ የኦሮሚያ ፓሊስ እና የፌዴራል ፓሊስ ተኩስከፍቷል ተብሏል። ከመንግስት ጥቃት ይደርስብኛል በማለትስማቸዉ እንዳይገለጽ የጠየቁ ከኦሮሚያ ና የፌደራል ፖሊስበተጨማሪ የአግአዚ ታጣቂዎች ገብተዉ አመል የሚባልየተማሪዎች መኖሪያ ሕንጻ የሚገኝበት ግቢ ዉስጥ ከምሽቱ 4 ሰዓትየጀመሩ እስከ 11 ሰዓት ድረስ ሲቀጠቅጡዋቸዉ ነበር ብለዋል።ብዙ በጽኑ የቆሰሉ ተማሪዎች መኖራቸዉ ቢታወቅም በዉልአጣርተን ማንነቱን አላወቅንም እንጂ የሞተ ተማሪ እንዳለይነገራል ብለዋል።

ሌላ እንዲሁ የዓይን እማኝ መሆናቸዉን የተናገሩ ዛሬ ማለዳበቴክኖሎጂ ካምፓስ ያሉ ተማሪዎች ከተሸሸጉበት ተሰብስበዉተቃዉሞ ለማድረግ ሲሞክሩ፤ ዉሃ በሚረጭ አድማ በታኝ መኪናእና በዱላ በመደብደብ ተማሪዎቹን እንደበተኑ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአለማያ ከተማ ያሉ የሁለተኛ ደረጃናየመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃዉሞ ሲያሰሙ፤ከተማዋን ተቆጣጥረዋት የነበሩ የአጋአዚ ሃይሎች ያገኙትን ሁሉእንደደበደቡ፣ በድብደባዉ 15 የሚሆኑ ሴቶች ተማሪዎች ከፍተኛጉዳት እንደደረሰባቸዉ ለአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ቃልዋን የሰጠችተማሪ ገልጻለች።

Posted By Aseged Tamene

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: