ኤርሚያስ አመልጋ የተገባላቸው ቃል ታጥፎ ለእስር ተዳረጉ

የተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች መስራችና የአክሰስ ሪል ስቴት ባለቤት የነበሩት ኢንተርፕርነሩ ኤርሚያስ አመልጋ በኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሰራተኞች መታሰራቸው ተሰምቷል፡፡በአሜሪካ የነበሩት ባለሐብቱ ከመንግስት ጋር በተደረገ ረዘም ያለ ጊዜ የወሰደ ድርድር እንደማይታሰሩና ያሉባቸውን ዕዳዎች ሰርተው እንደሚከፍሉ በመስማማታቸው በየካቲት ወር ወደ አገር ለመመለስ መብቃታቸው አይዘነጋም፡፡
የኢትዩጵያ ቴሌቭዥን እንደዘገበው ከሆነ የታሰሩት ኤርሚያስ ኪሳራ አጋጥሞታል ስለሚሉት አክሰስ ሪል ስቴትና መኖሪያ ቤቶችን ለማግኘት ቃል ተግብቶላቸው ክፍያ ስለተፈጸመባቸው ቤቶች ምርመራ ይደረጋል ፡፡
ባለፈው ዓመት ሪፖርተር ጋዜጣ የፍትህ ሚንስትር ምንጮችን በመጥቀስ አስፍሮት በነበረ ዘገባ ‹‹በኤርሚያስና በድርጅታቸው ላይ የቀረቡባቸው 81 ክሶች ለአንድ ዓመት ሳይንቀሳቀሱ እንደሚታገዱ፣ ያሉባቸውን ዕዳዎች እስከሚከፍሉና ቤቶቹን በተመለከተ የተፈጠረውን ውዝግብ እስኪፈቱ ለአንድ ዓመት የህግ ከለላ እንደሚያገኙ ››ጠቅሶ ነበር፡፡
በ2004 ኦዲተሮች ባቀረቡት ሪፖርት አክሰስ ሪል ስቴት ለቤት ገዢዎቹ ለማስተላለፍ ቃል በመግባት የተለያዩ ክፍያዎችን የተቀበለባቸውን ቤቶች የማቅረብ አቅም እንደሌለው አስታውቀው ነበር፡፡ሪፖርቱ በወጣ በአመቱ ኤርሚያስ ወደ ጎረቤት አገር ከዚያም ወደ አሜሪካ አቀኑ፡፡ባለሐብቱ በአሜሪካ ቆይታቸው የደምበኞቻቸውን ገንዘብ መብላት እንደማይፈልጉ በመጥቀስ ከእስር በመለስ እዳቸውን ለመክፈል የሚያስችሏቸው ሁኔታዎች እንዲፈጠሩላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡
ነገር ግን ኤርሚያስ በአሁኑ ወቅት ወደ አገር ለመመለስ ያስቻላቸው የተስፋ ቃል እንደጉም በኖባቸው አንዱን ዓመት ሳያገኙ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል፡፡ኤርሚያስ ወደ አሜሪካ ከማቅናታቸው ጥቂት ቀደም ብለው ከቼክ ጋር በተያያዘ ታስረው የነበሩ መሆኑ አይዘነጋም፡፡
በአሜሪካ ትምህርታቸውን ያከናወኑት ኤርሚያስ በአገሪቱ በፋይናንስ ኢንደስትሪ ውስጥ ለዓመታት ሰርተዋል፡፡በ1989 አካባቢ ወደ አገራቸው የራሳቸውን ካምፓኒዎች በመፍጠር ሰርተዋል፡፡ባለሐብቱ አዳዲስ ሐሳቦችን በማፍለቅ ፣ካምፓኒዎችን በመመስረትና በገንዘብ በመደገፍ ተለይተው ይታወቃሉ፡፡
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የታሸገ ውሃ አምራች ካምፓኒ ሐይላንድ ውሃ፣ አክሰስ ካፒታል፣አክሰስ ባንክና ጃኖ ባንድን በመመስረት ስማቸውን አስተዋውቀዋል፡፡የኤርሚያስ የመጀመሪያ ካምፓኒ ሮያል ክራውን የተፈጥሮ ውሃ ፋብሪካ በተመሰረተ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ እንዲዘጋ መደረጉ አይዘነጋም፡፡

Dawit Solomon Yemesgen's photo.
posted by Aseged Tamene
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: