ሳዑዲ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ አንገት ቀላች

ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ በሳዑዲ አሰሪዋን ገድላለች በመባሏ እሁድ ዕለት በሳዑዲዋ ታይፍ ግዛት አንገቷን መቀላቷን የአገር ውስጥ ሚንስትሩ አስታውቀዋል ።
የሞት ፍርዱ የዛሬ ዓመት በጥር ወር መተላለፉን ያስታወሰው አረብ ኒውስ ኢትዮጵያዊቷ ይግባኝ በመጠየቋ በዛ ያሉ ተከታታይ ቀጠሮዎች እየተሰጡ ጉዳዩ ሲታይ ቆይቷል ብሏል ።
ከሶስት ዓመት በፊት ያኒት ዳምጤ ፋሪድ ቀጣሪዋን በደቡብ ታይፍ ግዛት ሙሳዒላት መንደር በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ በድሁር ፀሎት ላይ እንዳለች ለስምንት ጊዜያት ያህል ጭንቅላቷን በመጥረቢያ በመምታት እንደገደለቻት ተነግሮ ነበር ።
የመካ ፖሊስ ቃል አቀባይ አቲ ቢን አቲያ በሰላሳዎቹ የዕድሜ መጀመሪያ ላይ ትገኝ የነበረችው ያኒት የአሰሪዋን ንብረት ለመዝረፍ በማሰብ ወንጀሉን ስለመፈፀሟ ያደረግነው ምርመራ ያሳያል ብለዋል ።ያኒት በተያዘችበት ወቅትም 7000 የሳዑዲ ገንዘብ እጇ ላይ ተገኝቷል ማለታቸው ተጠቅሷል ።
የሟቿ ባለቤት ጋሃሊያ ቢንት ሰዒድ ኢትዮጵያዊቷ ላይ በተላለፈው ውሳኔና ውሳኔውም በፍጥነት ተፈፃሚ በመሆኑ የተሰማውን ደስታ ገልጿል ።
ያኒት አሰሪዋን ገደለቻት? ለምን ገደለቻት?በወህኒ ቤት ቆይታዋ ምን ደርሶባታል፣ በተፈፀመባት ግርፊያ ቃልዋን እንድትሰጥ ተደርጋ ይሆን ? ጠበቃ ቆሞላታል?ኢምባሲው ወይም ያኒትን ከአገርዋ ያስወጣት የኮሚሽን ድርጅት ጉዳይዋን ተከታትሎ ይሆን ? ይቅርታ ለካ ይህ ጥያቄ ለኢትዮጵያዊ አይጠየቅም ።

Dawit Solomon Yemesgen's photo.posted by Aseged Tamene
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: