በሶማሊያ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በመስጠሟ 122 ሰዎች ሞቱ ኢትዮጵያዊያንም ይገኙበታል

በሰሜናዊቷ የሶማሊያ ግዛት ከሰጠመችው የስደተኞች ጀልባ ጋር ተያይዞ የሟቾቹ ቁጥር 122 ሊደርስ እንደሚችል የግዛቲቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያዊያንና ሱማሊያዊያን ስደተኞችን መጫኗ የሚነገርላት ጀልባ የሰጠመችው በሶማሌላንድ አካባቢ በሚገኝ ባህር ነው፡፡ በአደጋው 112 አስከሬኖች መገኘታቸውን የሚናገሩት ባለስልጣናት አስከሬን ፍለጋው በመቀጠሉ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል ማለታቸውን ኤስ ቢ ኤስ አስነብቧል፡፡
ባሳለፍነው አርብ ጀልባዋ ባጋጠማት የቴክኒክ ችግር ምክንያት ለመስጠም መብቃቷን የሚናገሩት የክልሉ የጤና ኃላፊ አብዱረህማን ያሲን ‹‹የባህሩ ጠባቂዎች የ75 ሰዎችን ህይወት ሲያተርፉ የአካባቢው ነዋሪዎች የ112 ሰዎችን አስከሬን ሰብስበዋል፡፡ባህሩ በአስከሬን ተሞልቶ ነበር››ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
ከአደጋው የተረፉትና ጉዳት የደረሰባቸው በአቅራቢያ ወደሚገኘው በርበራ ከተማ ወደሚገኝ ክሊኒኮች መወሰዳቸውም ተነግሯል፡፡
ሶስት የጀልባዋ ሰራተኞች አደጋው ከደረሰ በኋላ ሸሽተው ለማምለጥ ቢሞክሩም በአካባቢው በነበሩ ሰዎች መያዛቸውን የሳናግ ክልል ሊቀመንበር አህመድ አብዲ ፋላይ ተናግረዋል፡፡
በየዓመቱ ብዙ ሺህ ስደተኞች ወደ የመን ለማምራት ይህንን ባህር በአነስተኛ ጀልባ እንደሚያቋርጡ ያስታወሱት አህመድ እንዲህ አይነት አደጋዎችም በየጊዜው እንደሚስተዋሉ አስታውሰዋል፡፡
የመን ወደ አረብ አገራት ለሚሻገሩ ስደተኞችም እንደ ድልድይ ስታገለግል መቆየቷም ይነገራል፡፡ሶማሌዎች፣ኤርትራዊያንና ኢትዮጵያዊያን አነስተኞቹን ጀልባዎች እጅግ አስፈሪ በሆነ ሁኔታ እየተጠቀሙ የባህር ሲሳይ ሆነው ከሚቀሩት በዋናነት ይጠቀሳሉም ተብሏል፡፡

Dawit Solomon Yemesgen's photo.

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: