በሳዑዲ 129 ኢትዩጵያዊያን የገናን በዓል ሲያከብሩ ተይዘዋል

የሳዑዲው አከህባር 24.ኮም (AKHBAAR24) እንደዘገበው ከሆነ ትናንት (አርብ ምሽት ) በጃዛን አካባቢ የሚገኝን የአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በመክበብ ፍተሻ ያደረገው የአገሪቱ የወንጀል ምርመራ ፖሊስ 129 አፍሪካዊያንን ለመጠጥነት ከተዘጋጁ የተለያዩ አይነት የአልኮል ምርቶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን በምስል አስደግፉ አስነብቧል፡፡ከተያዙት ውስጥ 41ዱ ሴቶች ነበሩ ብሏል፡፡
የጃዛን ክልል ፖሊስ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሙሐመድ ሃርቢ 129 አፍሪካዊያን በቤት አሰሳው ወቅት መያዛቸውን አረጋግጠዋል፡፡ኮሎኔሉ ከአፍሪካዊያኑ ጋር የተገኘውን የአልኮል መጠን ይፋ ለማድረግ ገና ምርመራ በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ ቢገልጹም አንድ ሺህ ሊትር የሚሆን ከጂንና ከጭማቂ የተዘጋጀ ጠንካራ የአልኮል መጠጥ ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
አፍሪካዊያኑ በምን ምክንያት በአንድ ሰው መኖሪያ ቤት ውስጥ በብዛት ሊሰባሰቡ እንደቻሉ የዜናው ምንጭ ባይጠቅስም በኢትዩጵያ የክርስቶስ ልደት እየተከበረ በመሆኑና የሰዎቹ ምስል የኢትዩጵያዊያንን ስለሚመስል ሰዎቹ በዓሉን ለማክበር የተሰባሰቡ ሳይሆኑ እንዳልቀሩ መገመት አያስቸግርም፡፡
በሳዑዲ መጠጥ በጥብቅ የተከለከለ በመሆኑም በሰዎቹ ላይ ሊተላለፍ የሚችለው ቅጣት ከፍተኛ ሊሆን ይችላል፡፡በቅርቡ የአገሪቱ ሐይማኖታዊ ፍርድ ቤት አልኮል ሲሸጡ ተያዙ በተባሉ አራት እንግሊዛዊያን ላይ የሁለት አመት እስራትና የ500 የጅራፍ ግርፋት ወስኖባቸዋል፡፡

posted by Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to በሳዑዲ 129 ኢትዩጵያዊያን የገናን በዓል ሲያከብሩ ተይዘዋል

  1. Pingback: በሳዑዲ 129 ኢትዩጵያዊያን የገናን በዓል ሲያከብሩ ተይዘዋል - EthioExplorer.com

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: