“መለሰ ዜናዉ እስከሞተበት ቀን ድረስ በአካልና በስልክ እንገናኝ ነበረ” ሌንጮ ለታ

ሌንጮ ለታ

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር፣ ለአማራ ሕዝብ ደግሞ እንደ ሕዝብ ከትግሬ ወያኔ የከፋ ጠላት የላቸዉም። በተለይ ለአማራ ሕዝብ በአይነቱም ይሁን በመጠኑ ህዉሃት የፈፀመበትን አይነት ዘግናኝ ግፍ የፈፀመበት የለም። ስለዚህ “ከማያዉቁት መለአክ የሚያዉቁት ሰይጣን ይሻላላ” የሚለዉን የአበዉ አባባል ዛሬ ላይ መዝለል ግድ ይላል። ሰሞንን ለተነሳዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ የሚሰነዘሩት ማስፈራሪያዎች የመጀመሪያዉ ህወሃት ከወረደ ሀገር ይፈርሳል? የሚል ነዉ። አዉንስ ምን ሀገር አለንና ነዉ? ሀገር ከፈረሰ 25 ዓመቱ ነዉ። ሁለተኛዉ ደግሞ ህወሃት ከወረደ ብሔር ተኮር ግጭት ሊፈጠር ይችላል? እሽ ተከሰተ እንበል፤ ምን ይከተላል? መፈናቀል?፣ መሰደድ?፣ መደፈር?፣ መዋረድ?፣ ሀብት ንብረትን መዘረፍ?፣ ሕይወትን ማጣት?፣ በአዉሬምና በሰዉ ታርዶ መበላት? አይደል የሚደርስብን? እስኪ ከነዚህ ግፎች ዉስጥ አማራ ላይ ያልደረሰ የትኛዉ ነዉ? ባጭሩ ምንም የለም። ብርቅ አይደለም። እኔ እስከማዉቀዉ ድረስ አማራ ጠል የሆኑ የዉጭም (እንደ ኢጣልያ ያለ) የዉስጥም (እንደ ኦነገ ያለ) አይነት ጠላቶች ቢከሰቱም፤ የአማራን ዘር ጨርሰን አጥፍተን ታሪክ እናደርገዋለን ፣ ከዛም እርስቱን ነጥቀን የኛን ትዉልዶች እንተክላለን ብለዉ ካርታ ቀርፀዉ፤ ለተግባራዊነቱ የታተሩና በሚሊዮን የሚቆጠር አማራ ያጠፉ፤ በተጨባጭ የምናዉቀዉ ትግሬ- ወያኔዎችን ነዉ። ስለዚህ ህዉሃትን የሚያደባይ የትኛዉም ሀይል ቢመጣ ከተቻለ መደገፍ እንጂ መቃወም ወይንም ከህዉሃት ጎን መቆም የማይታሰብ ነዉ። አርባ አራት ነጥብ። ስለዚህ የዚህ መጣጥፍ አላማ ሰሞኑን እየተካሄደ ያለዉን እንቅስቃሴ ለመቃወም አይደለም ። አላማዉ ከዛጋ ተያይዞ አንድ አንድ ፀረ አማራ የሆኑ ሰዎችና ትናንት ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ ፀረ ኢትዮጵያም የነበሩ ሰዎች በአንድ ሳምንት ዉስጥ ተገልብጠዉ ፣ ከጀርባ ላነገቱት አላማቸው ብቻ ሲሉ ኢትዮጵያዊ ማንነትን ለብሰዉ እየሄዱበት ያለዉን ፀያፍ አካሄድ ለመተቸት ነዉ።

>>>ሌንጮ ለታ

አንዳንዴ “ክፉ ሰዉ እድሜዉ እርጅም ነዉ” የሚለዉ አባባል እዉነት ይመስለኛል። ለምሳሌ ሊትል ቦይን (Little Boy) እንደ አዉሮፖዎች የዘመን አቆጣጠር ነሀሴ 6/ 1945 ዓ.ም ሄሮሽማን ላይ ጥሎ፤ በሰከንድ ዉስጥ ወደ 80,000 ሺህ የሚጠጉ ንፁህ ጃፓናዊያንን የፈጀዉ እና ከዚህ ቁጥር በላይ ለሆኑ ሰዉች አካል መጉደል ምክንያት የሆነዉ አሜሪካዊው ፓይለት Paul W. Tibbets፤ እድሜዉን ጥጥት አድርጎ ዘጠናዎችን አጋምሶ ነዉ የሞተዉ። ሊሞት አንድ ሳምንት ቀርቶት፤ ጃጅቶ ስለተሰጠዉ ግዳጅና ስለቀጠፈዉ የሰዉ ሕይወት ሲጠየቅ፤ ቅንጣት ታህል ሀዘን እንደማሰማዉ፤ ዛሬ ተመሳሳይ ግዳጅ ቢሰጥህስ በደስታ ግዳጁን እንደሚወጣ ነበር በድፍረት የተናገረዉ። ወታደር ስለሆነ ግዳጁን ሐፈፀም ነበረበት ምናምን የሚል ክርክር ሊነሳ ይችላል። ለኔ ግን ወታደርም ሰዉ ነዉ። ስሜት አለዉ። ግደል ስለተባለ ብቻ አንደኛዎቹ አጋዚዎች ቃታ መሳብ ያለበት አይመስለኝም። ለማንኛዉም ሌሎች መሰል ጨካኝና ክፉ ሰወች እንዲሁ መጥቀስ ይቻላል።

ወደኛዋ ሀገር ስንመጣ ደግሞ በግለሰብ ደረጃ ዛሬ ላለንበት አጣብቂኝ ሁኔታና በተለይ ደግሞ ባለፉት 25 ዓመታት ለተጨፈጨፉት ወደ 5 ሚሊዬን ለሚጠጉ የአማራ ወገኖች ዋና የጥፋት አርክቴክት የሆኑት እነ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ስብሐት ነጋ፣ አባይ ፀሀየ፣ ሌንጮ ለታ አይነት ክፉ፣ ሸረኛ ሰዎችን ዛሬ ድርስ ከነሙሉ ክፋታቸዉ በሕይወት አሉ። የጃቸዉን የሚሰጥ ጠፍቶ፣ አንደ ማንም ንፁህ ሰዉ የእግዚያቤሄርን ሞት እየጠበቁ ነዉ። ምናልባትን እንደ መለስ በሞታቸዉ ሀገር በትዛዝ ማቅ ይለብስም ይሆናል።

ወደዋናዉ ሀሳቤ ልመለስና በቅርቡ የኦነጉ አባት ሌንጮ ለታ ከኢሳት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር ባደረገዉ የተጠናና የተመጠነ ቃለ መጠየቅ፤ በርካታ ሀሳቦች የተነሱ ቢሆንም ሶሥቱን አንምዘዝ።

1. ስለ ቻርተሩ አቀራረፅ ለተጠየቀዉ ጥያቄ ሌንጮ እንዲህ ይለናል፦

“ኢሳያስ መለስ እና እኔን ጠርተዉ ኢትዮጵያ ላይ ከዚህ በኋላ ስለሚደረገዉ ነገርና ስለ ኤርትራ ጉዳይ እንወያይ የሚል ሀሳብ አቀረበ። ኤርትራ ተሰኔ ላይ ተገናኝተን ሶስታችንም ሀሳብ አቀረብን ። እኔ ባነሳሁት ሀሳብ ላይ በመመስረት የቻርተሩ እረቂቅ ተፃፈ። በኋላ ያዉ ከማሻሻያ ጋር አዲስ አበባ ላይ ፀና ”።

እንግዲህ እናስተዉል። ይህ ግለሰብ ከ1983 ዓም በፊት በነበረዉ የጫካ ቆይታ ፤ የዉሸት በተለይ አማራና ኢትዮጵያ ጠል የሆኑ ድርሰቶችን እየደረሰ የኦሮሞዉን ትዉልድ በጥላቻ ኮትኩቶ ያሳደገ ሰዉ ነዉ። ጅዋርን የመሰለ የሜንጫ ፓለቲከኞችን ፣ እንዲሁም በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች እንዳዳመጥነዉ ዛሬ “አቢሲኒያች ጥቁር ይጠላሉ እያሉ” ዓለም አቀፍ ጠላት እየገዙልን ያሉ ለታሪክ ጠንጋራ አመለካከት ያላቸዉን ወጣቱ ፕ/ሮች የሌንጮ የጫካ ፓለቲካ ዉጤት ናቸዉ። እዚህጋ ማስተዋል የሚያስፈልገዉ እንግዲህ ተማርኩ የሚሉት ይህን መሰል የፖለቲካ ስብህና ካላቸዉ፤ በነሱ ደረጃ ያልደረሱና ፊደል ያልቆጠሩት ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት አይከብድም። በተግባርም እፃን አረደዉ አሳይተዉናል።

ሌንጮ ለታ ተሰኔ ዉስጥ ኢትዮጵያን የሚያፈረሰዉን ቻርተር ብቻ አይደለም የቀረፀዉ፤ ዛሬ ከራሱ አንደበት እንደሰማነዉ፤ የመለስ እስትንፋስ እስከምትቋረጥ ድረስ ከመለስ ጋር ሀሳብ ይለዋወጥ የነበረ ሰዉ ነዉ። ስለዚህም በባለፉት 23 የመከራ ዓመታት መለስ ይፈፅመዉ ለነበረዉ ግፍ ሀሳብ በማመንጨት ይረዳዉ ነበር ማለት ነዉ። ኢትዮጵያ ቋንቋን መሰረት ባደረገ የክልል አወቃቀር እንድትዋቀር፣ አወቃቀሩም ከአማራ መሬት ወደ ትግራይ፣ ወደ ኦሮሚያ ፣ወደ አፋር እንዲቆረስ፣ ከአማራ መሬት ተቆርሶ ቤንሻንጉል ጉምዝ የተባለ ክልል እንዲካለል፣ ከዛም አልፎ አስጠግተዉት ለነበሩት ሱዳኖች የጎንደር መሬት ተገምሶ እጅ መንሻ እንዲሰጣቸዉ ሀሳብ ሲያመነጭ የነበረ መርዝ ግለሰብ ነዉ። ኦነግ በአሰቦት ገዳም፣ በአርባ ጉጉ፣ በወተር፣ በበደኖ በሌሎችም የሐረርጌ እና አርሲ አካባቢዎች ይኖሩ በነበሩ ዐማሮች ላይ የፈፀሙት የግፍ ጭፍጨፋ፤ በወለጋ፣ በኢሉባቡር፣ በጅማ ያካሄዷቸው ዐማራን በጅምላ የመግደል ዘመቻዎች፤ ሌንጮ ዋናዉ ተጠያቂ ነዉ።

ዛሬም ቢሆን ከየቦታዉ ተዋርደዉ ለሚፈናቀሉት፣ ሀብት ንብረታቸዉ በጠራራ ፀሀይ ለሚዘረፉት፣ ለሚገደሉትና ታርደዉ ለተበሉት አማራዎች፣ ሀሳብ ያዋጣ፣ መሰረት የጣለ ፣ የአማራ የምንግዜም ጠላት የሆነ አረመኔ ሰዉ ነዉ።ባጠቃላይ ኢትዮጵያም ሆነች አማራ ሕዝብ ዛሬ ላለንበት ደረጃ ለመድረስ ከህዉሃት ሰዎች አኩል እንደዚህ ግለሰብ ተጠያቂ የሚሆን አካል የለም።

2. ኢትዮጵያን በተመለከተ ደግሞ ሌንጮ እንዲህ ይለናል፦

“ኢትዮጵያዊነት የሚባለዉን የሚያነሱት ሀይሎች ትልቅ አላፊነት አለባቸዉ። ኢትዮጵያዊነት እዉነት ካለ፤ ኦሮሞም እዛ ዉስጥ የሚገኝ ከሆነ፤ ለኢትዮጵያዊነት የሚሟገት ሁሉም ለኦሮሞ በቻለ መንገድ መድረስ አለበት።”

ይህንን መሰል ሀሳብ እንግዲህ ሰሞኑን ሲሰነዘር የሚደመጠዉ ከሌንጮ ብቻ አይደለም። ጅዋርን ጨምሮ ኢትዮጵያን አምረዉ ይጠሉ ከነበሩ በረካታ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ሲደጋግሙት የሚደመጠ አስቂኝ “ማስፈራሪያ” ነዉ። እንደዉም በሚገርም ሁኔታ ኤርትራዊ-ኦሮሞዉ ተስፋየ ገብረአብ ሳይቀር ሰሞኑን በለቀቀዉ መጣጥፍ እንዲህ ይለናል” “በዚህ ወቅት ከኦሮሞ ህዝብ ጎን አለመቆም የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያዊነት ማእቀፍ ስር ለመኖር ያለውን ጥቂት ተስፋ መግደል መሆኑን የማይገነዘብ ፖለቲከኛ ኢትዮጵያን ወደ ገሃነመ እሳት ለመጨመር እንደተባበረ ማወቅ አለበት።”

እንግዲህ ተመልከቱ፣ ሌንጮ ለታ ለ40 ዓመታት ሲታትር የኖረዉ ኢትዮጵያን አፍርሶ ኦሮሚያ የሚባል ሀገር ባለቤት ለመሆን ነዉ። ለዚህም ድካሙ የዛሬ 25 ዓመት ተሳክቶለት ኤርትራን አስገንጥሎ፣ ኢትዮጵያን የሚያፈረሰዉን ቻርተር ተክሎል። ግልገሎቹ እነ ጀዋር ደግሞ ላለፋት 25 ዓመታት ለተግባራዉነቱ ሜንጫቸዉን ሲያወናጭፉ ነዉ የከረሙት። የአንድነቱ ጎራ “ተዉ አብሮነቱ” ይበጀናል ሲል፤ ጅዋራዊያን እነ ሌንጮ የደረሱላቸውን የዉሸትና የጥላቻ ቱሪናፋቸዉን ሲነፉ ነዉ የባጁት። የአንድነቱ ጎራ እባካችሁ ይህንን ህዉሃት የሚባል አናሳ፣ ሌባ፣ መሰሪ ቡድን ጥለን የጋራ ዲሞክራሲያዊት የሆነች ሀገር እንመስርት ሲባል፣ አሻፈረኝ ብለዉ ብዙ ወገኖቻችንን አፈናቀሉ፣ ዘረፉ ፣ገደሉ፣ የተስፋየ ገ/ዓብ ተረት ተረት ላይ ተመስርተዉ የጥላቻ ሀዉልት ተከሉ፣ ለኢትዮጵያዊ አንድነት፣ ስለፍቅር እያቀንቅነ ላሉዉ ከያኒ ካምፔን (ፒቲሽን) አሰባስበዉ ዉጤታማ ሆኑ። ይህ እንግዲህ ድሮ ሳይሆን ትላንት ነዉ። እና እነዚህ ወገኖች ዛሬ ኢትዮጵያዊነት በአንድ ሳምንት ተገልጦላቸዉ ነዉ አቦራ የሚያጨሱት? ቢሆንስ አማራ ላለፉት 25 ዓመታት በህዉሃት አሳሩን ሲበላ ዳር ቆሞ ሲያይ፣ አልፎ አልፎም ሲተባበርና በደስታ ብርጭቆ ሲያጋጩ ፣ ሲዘባበቱ የከረሙ የኦሮሞ ኢሊት፣ እችን ሁለት ሳምንት ህዉሃት ቆነጠጠን ብለዉ የአንድነቱ ካምፕ ካልደረሰልን ለኢትዮጵያ አደጋ አለዉ ብሎ መጮኸ ምን አይነት ድንቁርና ነዉ? ምን የሚሉት ድፍረት ነዉ።

ሂድ አልፈልግህም ብለህ ፤ ነፋጠኛ፣ትምክተኛ እያልክ ስታሸማቅቀዉ፣ እንደ አዉሬ ስታድነዉ፣ ስትዘርፈዉ፣ ስደብድበዉ፣ ስታዋርደዉ፣ ስታርደዉ፣ ቆዳዉን ስትገፈዉ፣ ወደ ገደል ስትከተዉ የባጀኸዉን አማራ፣ ዛሬ ህዉሃት ቆነጥጦኛልና ከጎኔ ካልቆምክ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች አይነት ማስፈራራት ምን አመጣዉ። መቼ ያበደርከዉን ነዉ ዛሬ መልስ የምትሻዉ? ምንስ አዲስ የአቋምና የአስተሳሰብ ለዉጥ አቅርበህ ነዉ ግፍህና ወንጀልህ ተረስቶ፤ ከበረካታ አመታት በፊት ያፈረስከዉን ሀገር አማራ ዳግም እንዲሰራልህ የምትማፀነዉ? አማራ ትላንት ለአብሮነቱ ደሙን ላፈሰሰበት፣ አጥንቱን ለከሰከሰበት የተከፈለው ምን ሆነና ነዉ? ዛሬ ከአንተ ከአፍራሹ ጋር አብሮ እንዲሞት ሞቴን ሙትልኝ አይነት ግብዣ? ለናንተ እንጂ ለኛኮ ሞት የእለት ተለት ዉሎና አዳራችን ነዉ። እንደዉም ለምደነዉ እንደናንተ ስላልጮህን ነዉ እንጂ ያ ትላንት ተሰኔ ላይ አማራን ላማጥፋት የቀበርከዉ ቦንብ ፈንድቶ፤ ዛሬ እኛም ሰፈር የተለመደዉ ሞት፣ እሳት አለ። እንደናንተ በቆመጥ ከፖሊስ ጋር ሳይሆን መድፍና መትረየስ ከታጠቀዉ ከህዉሃት ሰራዊት ጋር። ስለዚህ ማስፈራራቱን ትተህ መክት። ትግላችሁ የነፃነት ከሆነ፣ አማራ ለምታደርጉት የነፃነት ትግል ከወደርኛቻችሁ ጋር አይሰለፍም፣ የኛ መገደል ባያሳምማችሁም፣ አልፎ አልፎም ተሳታፊ ብትሆኑም እኛ ግን ህመማችሁ በኛም የደረሰና የባጀንበት ነዉና ያመናል፣ ከገዳያችሁ ጎን አንቆምም። ቢቻል ህዉሃት የጋራ ጠላታችን ስለሆነ የጋራ አጀንዳ ቀርፆ የተጠና ትብብር ለማድረግ ነገሮችን ማመቻቸት እንጂ በጨበጣ ሞቴን ሙትልኝ እያሉ አቦራ ማጨስ የሞኝ ለቅሶ ነዉ።

3. ሌላዉና በጣም የሚያሳዝነዉ የሌንጮ መልክት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ያስተላለፈዉ መልእክቱ ነዉ። አዲስ አበባ ዎችን እንዲህ ይላቸዋል፦

ትንንሽ ከተማዎች ከአዲስ አበባ ተቆርጠዉ ለረዥም ግዜ ሊኖሩ ይችላሉ ። አዲሳበባ ግን ከአካባቢዉ ተለይቶ ለቀናት ሊቆይ አይችልም። ለምን የአዲስ አበባ የሚጠጣዉ ዉሃ የሚመነጨዉ ከኦሮሚያ ነዉ፣ አልፎ የሚመጣዉ በኦሮምያ መሬት ላይ ነዉ። ከዉጪ የሚገባዉ ሸቀጥ በኦሮሚያ አልፎ ነዉ። ነዳጅ የሚገባዉ በኦሮሚያ አልፎ ነዉ። ስለዚህ በአካባቢ ኦሮሚያ ከተሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ጥቃት እና ወንጀል የአዲስ አበባን ነዋሪ አይመለከትም ማለት እራስን ማታለል ነዉ። ይመለከታችኾል። ቢያንስ ቅሬታቸዉን ማሰማት ግዜዉ አሁን ነዉ።”

ይህ የሌንጮ ሀሳብ ግለሰቡ ምን አይነት መርዝ መትፋት የሚችል መሰሪ ፖለቲከኛ መሆኑንና መለስ ሀገር ለማፍረስ ለሚወስዳቸዉ መሰሪ እርምጃወች የዚህን ግለሰብ ጭንቅላት እንደ ግብአት ይጠቀም እንደነበረ የሚያስረግጥ ነዉ። ከላይ የተሰነዘረዉ አስተያየት በአጭሩ ሲቀመጥ >>> ማስተር ፕላኑ ተግባራዊ ሆኖ ኦሮሚያ ለሁለት ተከፎሎ የመገንጠል እቅዱ እንዳይመክን የአዲስ አበባን ሕዝብ በረሀብና በጥም ቆልቶና አስገድዶ የትግሉ አካል ማድረግ የሚል መልክት ነዉ።

ሁሉም እንደሚያዉቀዉ የአዲስ አበባ ነዋሪ ማለት በአንፃራዉነት የነቃ፣ የህዉሃትን ምንነት ጠንቅቆ የሚረዳ፣ የህወሃት ልክ የለሽ ስግብግብነትን አፍንጫዉ ስር ሆኖ የሚታዘብ፣ በ97 ምርጫ ወቅት ህዉሃትን አልፈልግህም፣ በቅታችሁናል ብሎ በአደባባይ ወጥቶ በድፍረት የተናገር፣ በተግባርም በምርጫዉ መቶ በመቶ ህዉሃትን የዘረረ ሕዝብ ነዉ።እንደዉም ህወሃት በሚያደርገዉ የመሬት ዘረፋ እንደ ከተማ ከታየ ከጎንደር፣ ወሎ፣ ጋምቤላ በመቀጠል የአዲስ አበባ ከተማ አንዱ ዋና ተጠቂ ከተማ ነዉ። ስለዚህ ከህዉሃት ጋር ለሚደረግ የነፃነት ትግል መርዙ ሌንጮ ለታ እንደሚነግረን ይህን ሕዝብ ላማስገደድ ጉሮሮዉ ላይ መቆም አይጠበቅብህም። እንደዉም ይሄ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ መንገዶችን መዝጋት የሚለዉ የትግል ስልት እንደሚነገረዉ የፌደራል ፖሊሶች እንቅስቃሴ ወደ ሚደረግባቸዉ የኦሮሚያ ከተሞች እንዳይገቡ ሳይሆን የአዲስ አበባን ሕዝብ በረሀብና በጥም አስገድዶ የትግሉ አካል ለማድረግ የሚደረግ ደባ ነዉ ማለት ነዉ። ይህ ደሞ ግለሰቡ የክልሎች አከላለል ላይ ዋና አርክቴክት ከመሆኑ ጋር ሲደመር፤ ቀድሞዉንም ኦሮምያ አሁን ባለዉ ቅርፅ እንዲከለልና የአዲስ አበባ በኦሮሞ ከተሞች እንድትከበብ መደረጉ ለዚህ መሰል እንቅስቃሴ የታቀደ ያስመስለዋል። ሌላዉ ነገስ የሚል ጥያቄ እንዲፈጠርና የማስተር ፕላኑ ጉዳይ የመዉጫ መንገድ ተደርጎ እንዲታሰብና የተነሳዉ ግርግር መደገፉ በአንገት ላይ ገመድ እንደማጥለቅ ሆኖ እንዲታይ ያደርገዋል ማለት ነዉ።

ማጠቃላይያ
**********
አገር የሰሩ አባቶች አንደነ ሌንጮ እንዲህ ካላረክ አብረን አንኖርም ምንትሴ እያሉ እያስፈራሩ አልነበረም። እንደነ መለስ ዜናዊና ሌንጮ ግዜ ሰጥቶናል ብለዉ አርቄ ቀበርኮችሁ፣ አከርካሪያችሁን ሰበርኩ፣ ዉጡልኝ ፣ ከአሁን በኋላ ሳር ቅጠሉ ለኔና ለዘሮቼ ብቻ ነዉ እያሉና የሌላ ነዉ ብለዉ የሚያስቡትን ሲዘርፉና ሲያዘርፋ፣ ፊንፊኔ ኬኛ ( Fiinfinnen keenyaa)፣ ምንትስ ኬኛ ማለታቸዉን አላነበብንም ።ጥቂት እዉነት ቀመስ የታሪክ ጠባሳዎች ላይ ተራራ የሚያህል ዉሸት ቆልሎ ጥላቻን ሲዘምሩ አልሰማንም የቆሙትንም የጥላቻ ሀውልት አላየንም።

አገር የሰሩ አባቶች በስልጣኔ፣ በባህል፣ በቋንቋ፣ በአመለካከት ተለያይቶ የነበረን ማሕበረሰብ አሰባስቦና አስማምቶ በአንድ አስተዳደር ዉስጥ እንዲኖር ሲደክሙ፤ በታሪክ አጋጣሚ አንደኛዉ ጎሳ ሌላኛዉ ላይ የፈፀመዉን ዘግናኝ ጭፎጨፋ፣ ወደጎን ገፍቶና ይቅር አባብሎ ዋሽተዉ ሲያስታርቁ፤ ጎባጣ ጎባጣዉን የታሪክ ኩነት ሆን ብሎ እየዘለሉ፣ ለመጭዉ ትዉልድ በጎበጎዉን ፍቅርን ሲያወርሱ ነዉ የምናዉቀዉ። ሊገላቸዉ ጦር የሰበቀ፣ሰይፍ የመዘዘ ጠላታቸዉን ማረከዉ በእጃቸዉ ከወደቀ በኋላ፣ ጎንበስ ብለዉ እግሩን አጥበዉ፣ ቁስሉን አስታመዉ፣ በመልካም እንክብካቤ አስተናግዶዉ፣ ሸልመዉ ከነሙሉ ክብሩ፣ ከነ ጦሩ ወደ እርስተ ጉልቱ የመመለስን ቅንነት እንደነበራቸዉ ነዉ ያነበብነዉ። ልምድና ባህልላቸዉን ሲቸሩ፣ የነሱ ብቻ የነበርን ለሌሎች ሲያካፈሉ፣ ለሁላችንም ይበቃናል፣ ተካፍለን መኖእርዉ እቀንትች፣ላለ ሲሉ እንደነበር ነዉ የታዘብነዉ።

ለማንኛም እናንተ ዛሬም እንደትላንቱ የማጭበርበርና የተንኮል ጉርብትና ነዉ እያቀነቀናችሁ ያላሁት። አንዳች የአመለካከትም ሆነ የአቆም ለዉጥ ባልታየበት ባዶ ጫጫታ፣ ኑና ሞቴን ሙቱልኝ፣ ድረሱልኝ ያለዚያ ኢትዮጵያ ትፈረሳለች እያሉ ማላገጥ ትረጉም የለሽ ጥሪ ነዉና ጥሪህንና መስመርህን መርምር። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በሰዎች ልብ ዉስጥ ካልሆነ በቀር በአካል ከፈረሰ 25 ዓመት አልፎታል ። ዛሬ መንፈስ እንጂ አካላዊ አይደለም።

ግዜነዉ ደም መላሽ

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

9 Responses to “መለሰ ዜናዉ እስከሞተበት ቀን ድረስ በአካልና በስልክ እንገናኝ ነበረ” ሌንጮ ለታ

 1. Morkii says:

  You don’t understand why Oromo struggle is so powerful also why the world interested in because we are on the way for justice democracy, to build very brief country. truth always the winner. You cannot even blame Jawar people of amhara understood him well and we are now living together. dont try to make a confusion to stay on power you cannot foolish us any more. Future is going to ask you why …….?

  Like

 2. You are so stupid. When the Amhara extended its discriminatory apartheid and dehumanizing policy it is is unity and love. Every Ethiopian recall how the Amhara used to dehumanize the Ethiopians using derogatory words against the B. Gumuz (used call shankilla), Oromo (used to call Galla), Tigrae (Used to call Tsila), SNNP (used to calll welamo). Amhara are such a people who are advocating the Unity of Ethiopia in the midst of old day political dream and nostalgia.
  But when the Oromo and others demand their god given freedom that is crime and disintegration of unity. Oromo and other have no intention to invade the Amhara lannd but it is the Amhara who always dream to invade others land under the banar of Ethiopian Unity. Do you think that Ethiopian people are kid to accept your indoctrination for grant. Do you have a mind to think that freedom is more than unity. All the cause of Oromo is to build Oromia. What is the crime with that? please tell me……………….. Of course Oromo are Ethiopia as Ethiopia is biblically the land of Kush and Oromo is also one of the major kush…..”As kush is the historical owner of Ethiopia so is the Oromo”, what you have to know!!!1

  Like

 3. yonatan abebe says:

  ok you are the most thought people for ethiopian unity

  your idea is clear and clear you want to create only one language in ethiopia

  your idea is also the “ye te chekone ye amara hizbi new meretu yetezerfew ye amhara new yalkew”

  any way what ever you say we oromo no need any help from amhara

  and first free yourself and correct yourself

  you not represent amhara peaple

  we will see the future

  Like

 4. Abdi Bilisuma says:

  You don’t know what you talk man. It is just from your nightmare, not from the reality on the ground. What if you drop your poisonous hatred on Oromo politicians and speculate the realities of the past, how they happened and in what conditions. You are not better than the TPLF with this mind and blocking the Oromo community not to ready this freedom4ethiopia. Long live Truth with Oromo People!!

  Like

 5. T K says:

  Dude, what are you talking about? It looks like you are saying the Oromo elites do not like other ethnicities. This is totally wrong and trying to divert the problem from the source to the victims. Try to make good analysis based on data and facts rather than just vomiting your hatred speech. Oromos(including educated Oromos) love the different ethnic groups in Ethiopia. That is why their land is a home for everyone(probably including you).

  Like

 6. Ermias Barii says:

  የዋህ መሃል ሰፋሪዎች ያነሱትን የእርስ በርስ እንደጋገፍ ፤ እንተባበር ጥሪ ጫፍ ሰፋሪዎች በሌላ መልክ ተርጉመው ለቅስቀሳ እየተጠቀሙበት ያለ ይመስለኛል።
  መሃል ሰፋሪው ማን ነው? ሠላም እና አብሮ መኖርን አበክረው የሚፈልጉ፤ በእኩልነት የምያምኑ የአማራው ፤ የኦሮሞው ፤ እና የሌሎችም ብሐሮች አባላት ናቸው።
  ጫፍ ሰፋሪውስ ማን ነዉ? የራሴን ብሐር ፤ ቋንቋ ፤ ባህል እና ጥቅም ብቻ ላስከብር የሌላው አያገባኝም የሚል የአማራው ፤ የኦሮሞው ፤ እና የሌሎችም ብሐሮች አባላት ናቸው። ለምሳሌም ያክል ፤ ወያኔ ፤ ሌንጮ ለታ ወዘተ..… የዚህ ጽሁፍ አቅራቢም በጽሁፉ ላይ ካነሳቸዉ አስተያየቶች አንጻር፤ በዚሁ ቡድን ውስጥ የሚካተት ይመስለኛል።

  Like

 7. jcfiig says:

  Dhama’aa

  Like

 8. abdi says:

  hed ante woshetam antem belo tsehafe
  ka yohannes,tewderos ena haylesillase say qer
  ye oromon sega setebaluna damun site tetut aydel ezeh yedarasachehut.

  Like

 9. Lammii Dhiiroo says:

  Asegid Tamene, I have been following what you try to write for the past few months. Currently I assured my self you are not an Amhara bigot, rather you are the regimes under table writer tr’n to seemingly simulate and tear your TPLF crocodile tears.

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: