ከቀድሞው የኢትዮጵያ የሀገር የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት አርበኞች ማህበር የቀረበ ወቅታዊ ጥሪ

በኢትዮጵያ የረጅም ታሪክ ውስጥ የሃገሪቷን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፎ ለመስጠት የተደራደረ መንግስት ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ፣ ሃገሩንና ድንበሩን እንዲጠብቅ አደራ የተሰጠውም ወታደርና የፖሊስ ሠራዊት የዚህ እኩይ ተግባር ተባባሪ የሆነበት ዘመን አልታየም።
ከሁሉም በላይ የህውሃት አቀንቃኝ ካድሪዎች በየጊዜው ከሚጎነጉኑት የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የሃገሪቷን ታላላቅ ብሄረሰቦች እርስ በርስ በማናቆር የጥላቻ ዘር በማህከላቸው በመበተን ስልጣኑን ለማራዘም ሁነኛ መሳሪያ አድርጎት ይገኛል። እንደእኛ እምነት ይህ ተንኮል በርግጥም ይህን ግፈኛ ሥርዓት ሃያ አምስት ዓመት እንዲቆይ ረድቶታል ብለን እናምናለን።
ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ይህ ሥርዓት በሃገራችን ታላላቅ ሃይማኖት መሃከል ጣልቃ በመግባት ለራሱ መሰሪ ተግባር በሚያመች መልኩ በማዋቀርና የሃይማኖት መሪዎችን በማሰር፣ በማንገላታት ፣ በመግረፍንና ብሎም ለስደት በመዳረግ የሃይማኖት ነፃነትን ገፏል ።
በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ሃይሎችንም በማሰርና በመግደል የቀሩትንም እንዲሰደዱ በማድረግ ድርጅቶቻቸውን በማፍረስ ህዝባችን ለሰላም ያለውን ተስፋ እንዲጨልምበት አድርጓል በማድረግም ላይ ይገኛል።
በከተሞች ልማት ስም ህዝቦችን ከቀያቸውና ከመሬታቸው በማፈናቀል ለውጭና ለሃገር ውስጥ ቱጃሮች መሬት በመሸጥ ህዝቡን ለእንግልትና ለስደት ዳርጎት ገበሬውን መሬቱን በመንጠቅ ለጐዳና ተዳዳሪነት ሲዳርግ ፤ ብሶቱንም በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት የወጣውን ህዝብ ደግሞ በጥይት መደብደቡን ተያይዞታል ።
የመከላከያ ፣ የፖሊስና የደህንነት አደረጃጀትና መዋቅር በአንድ አናሳ ብሔር የተያዘ በመሆኑ ፤ በስልጣን ተዋረድም ከላይ እስከ ታች በሙስና እንዲዘፈቁ ምቹ ሁኔታን በማመቻቸት ስርዓቱ ግለሰቦችን በሙስና እንዲከብሩና የአገሪቱ አንጡራ ሃብት እንዲባክን አድርገዋል ።

የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አርበኞች ማህበር በኦሮሚያ ክልል በፀጥታ ሃይሎች የተገደሉ ሰዎችን ድርጊት በማውገዝ የቀድሞ የሰራዊት አባላት ህዝቡ እያካሄደ ካለው ትግል ጎን እንዲሰልፍ ጥሪን አቀረበ። በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢህአዴግ መንግስት መብታቸውን በሚጠይቁ ሰዎች ላይ የሚወስደው የግፍ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጸው ማህበሩ፣ ህዝቡ ለሰላም ያለውን ተስፋም ጨልሞ እንደሚገኝ አስታውቋል። እያንዳንዱ የቀድሞ ሰራዊት አባላት በያለህበት ሆነህ በመደራጀትና በመቀናጀት እንዲሁም እርስ በእርስ በመናበብ የኢትዮጵያ ህዝብ እያካሄደ ካለው ትግል ጎን እንዲሰለፍ ሲል ማህበሩ ጥሪውን አቅርቧል። መቀመጫው በዚህ በአሜሪካ ያደረገው ይኸው ማህበር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ልዩነቱን በማስወገድና በመቻቻል የተጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥልም ሃሙስ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። በስልጣን ላይ ያለው ገዢው ኢህአዴግ መንግስት የሃገሪቱን መሬት አሳልፎ ለመስጠት ከሱዳን ጋር ያደረገው ድንበር የማካለል ስምምነት የሃገሪቱን ጥቅም የሚጎዳና ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አርበኞች ማህበር አክሎ ገልጿል። “የአገራችን መሬት ሲቆረስና ህዝባችን ሲጎዳም እጆቻችንን አጣምረን አንቀመጥም” ሲል የማህበሩ መግለጫ አመክቷል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: