የብሩንዲው ፕሬዚዳንት ፒሬ ነኩሩንዚዛ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ጦር ወደ አገራቸው የሚገባ ከሆነ እንደሚዋጉት ተናግረዋል ።

የብሩንዲው ፕሬዚዳንት ፒሬ ነኩሩንዚዛ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ጦር ወደ አገራቸው የሚገባ ከሆነ እንደሚዋጉት ተናግረዋል ።
የፕሬዝዳንቱ ማስፈራሪያ የተደመጠው የአፍሪካ ህብረት ያለ ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር መንግስት ፈቃድ 5000 ጦር ለመላክ መወሰኑን ማሳወቁን ተከትሎ ነው ።
ቢቢሲ በብሩንዲ ከሚያዚያ ወር ወዲህ 400 ሰው መገደሉንና 220.000 ሰዎች መፈናቀላቸውን ዘግቧል ። የአፍሪካ ህብረት ለዚህ ውሳኔ የበቃውም በዚህ መነሻነት እንደሆነ ይታመናል ።
ፕሬዘዳንቱ ባስተላለፉት ማስጠንቀቂያ የህብረቱ ጦር ያለ ፈቃዳቸው ድንበራቸውን ጥሶ የሚገባ ከሆነ እንዋጋዋለን ብለዋል።
“ሁሉም የብሩንዲን ድንበር ማክበር ይገባዋል ” ያሉት ነኩሩንዚዛ “የህብረቱ ጦር የሚገባ ከሆነም የምናየው ጥቃት እንደተፈፀመብን በመሆኑ ሁሉም ብሩንዲያዊ ይፋለማቸዋል” ብለዋል ።
በብሩንዲ ህገመንግስት መሰረት የውጪ ጦር ጣልቃ ሊገባ የሚችለው ጥያቄ ከአገር ውስጥ ሲቀርብ ወይም ህጋዊ መንግስት ስልጣን ላይ ከሌለ ብቻ ነው ማለታቸውን መንግስታዊው ራዲዮ አስደምጧል ።
ነኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ዙር በፕሬዘዳንታዊው ወንበር ለመቀመጥ ማሳወቃቸው በአገሪቱ ሁከት ቀስቅሷል ።ባለሞያዎችም ሁከቱ ተባብሶ ወደ እርስበርስ ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል ።
ፕሬዘዳንቱ የተቃጣባቸውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ባከሸፉ ሁለተኛ ወራቸው በሐምሌ ወር በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ የምርጫ ውድድር በከፍተኛ የድምፅ ልዩነት ማሸነፋቸውን ቢያስታውቁም የፕሬዘዳንትነት ዘመናቸው መጠናቀቁን የሚነግሯቸውን ተቃዋሚዎቻቸውን ለማሳመን አልቻሉም ።
(ጦር ወደ ብሩንዲ ልከው ዶላር ለመሸቀል ያሰፈሰፉ የአፍሪካ መሪዎች ምን አይነት ምላሽ ይኖራቸዋል ብለው ይገምታሉ ?)

posted by Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: