የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት ከፍተኛ አማካሪ ወንድም በህወሀት ወታደሮች ተገደሉ።

አቶ ዱጉማ እሬሶ የቶ ሙክታር ከዲር ከፍተኛ አማካሪ እና የከልሉ ‘የልማት ተቋማት ቢሮ’ ሃላፊ ናቸው። ወንድማቸው መ/ር አዱኛ በሆሮ ጉዱሩ ዞን ጃርዴጋ ወረዳ አሊቦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ምክትል ዳይሬክተር ነበሩ። ትላንት ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ በጀመሩ ጊዜ ወታደሮች አንድ ተማሪ ተኩሰው መተው ወደ ሌሎች መተኮስ ሲጀምሩ ጣልቃ ገብተው ይማጻናሉ። የወታደሮቹ መልስ ግን መምህሩን ከቢሮዋቸው ጎትተው አውጥተው ተማሪዎች ፊትለፊት ግንባራቸው አሏቸው። ሁለት ሌላ መምህራንም ተመተው ወደቁ። መ/ር አዱኛ ላጊዜው ህይወታቸው ተርፋ ወደ ሻምቡ ሆስፒታል ተወሰዱ፣ ካዚያም ወደ ጥቁር አንበሳ ረፈራል ተላኩ። ጥቁር አንበሳ ግን ለረጅም ሰአታት እንዲጠብቁ አደረገ። እየተጠባብቁም ሳለ አንዳች ህክምና ሳያገኙ ህይወታቸው እዛው መጣባበቂያ ክፍል አለፈች። በ አሁኑ ወቅት ሬሳቸው ውደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ተወስዷል። ትላንት ሙክታር ከዲር ነብሰ ገዳይ ወታደሮችን አመስግኖ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው የተገደሉትን ሲኮንን እንደ ነበር ይታወሳል:: ሞት የባለስልጣናቱንም በር ማንኳኳት ጀመረች።

posted by Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: