የዮናታን ቤተሰቦች ማዕከላዊን ሊከሱ ነው

የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ ዮናታን ተሥፋዬ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ ፍርድ ቤት ባለመቅረቡ፣ በወዳጅ ዘመዶቹ መጠየቅ አለመቻሉና ጠበቃ እንዲያማክር ባለመደረጉ ጭንቀት ውስጥ የገቡት ቤተሠቦቹ ሃፒየስ ኮርፐስን (አካልን ነጻ የማውጣት መብትን በመጠቀም) የዮናታንን አካላዊ እንቅስቃሴ የገደበውን ማዕከላዊን ለመክሰስ መዘጋጀታቸው ተሰምቷል፡፡
የዮናታን ወላጅ እናት በተደጋጋሚ ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢያመሩም “ፍርድ ቤት እሥከሚቀርብ ድረስ ወዳጅ ዘመድ ጋር መገናኘት እንደማይችል” ተነግሯቸዋል፡፡
ቤተሰቦቹ ዩናታን የሚገኝበትን ሁኔታ የማወቅ ፣ ጠበቃ እንዲያገኝና በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብቱ ሊከበርለት እንደሚገባ ቢገነዘቡም የማዕከላዊ ኃላፊዎች ውሳኔ ከአገሪቱ ህገ መንግስት በላይ ሆኖባቸው ላለፉት አራት ቀናት ምንም ማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡
ወላጅ እናቱ ልጃቸውን መጎብኘት አለመቻላቸውም በደህንነቱ ዙሪያ ስጋት እንደገባቸው መናገራቸው ተሰምቷል። ዮናታን በጸጥታ አካላት ከተያዘ አራት ቀናት ቢሆነውም አሳሪዎቹ እሥካሁን ፍርድ ቤት ያላቀረቡት ከመሆኑም በላይ መቼ እንደሚያቀርቡት ለመናገር ፈቃደኛ አይደሉም፡፡
ስጋት የገባቸው የዩናታን ቤተሰቦች በነገው እለት አካልን ነጻ የማውጣት ክሥ (የሃፒየስ ኮርፐስ ) ክስ እንደሚመሠርቱም ታውቋል፡፡

Dawit Solomon Yemesgen's photo.
posted by Aseged Tamene
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: