የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ መዉሰድ የጀመረዉ የእስረ ዘመቻ እንዳሳሰበዉ CPJ አስታወቀ

 

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል ተቀስቀሶ የነበረዉን ተቃዉሞ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ መዉሰድ የጀመረዉ የእስረ ዘመቻ እንዳሳሰበዉ መቀመጫዉን በዚህ በአሜሪካ ያደረገዉ CPJ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሰኞ አስታወቀ. በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ለእስር የተዳረገዉ ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፈራው በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ ተቋሙ ጥሪዉን አቅርቧል. በአንድ ሳምንት ዉስጥ ለእስር ሲዳረግ ሁለተኛ ጋዜጠኛ የሆነዉ ጌታቸዉ ሽፈራዉ, ባሳለፍነዉ አርብ ወደ ቢሮዉ በማምራት ላይ እንዳለ በጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን, ጋዜጠኛዉ በነገረ-ኢትዮጵያ ላይ በዋና አዘጋጅነት ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል. ጋዜጠኛዉ ቅዳሜ ፍርድ ቤት ቢቀርብም ፖሊስ ምርመራዉን አልጨረስኩም በሚል የ 28 ቀን የተጨማሪ የምርመራን ጊዜ ጠይቆ ፍርድ ቤት ይሁንታን ሰጥቷል. የጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፍራዉ እስር ግልጽ አለመሆኑን ያስታወቀዉ CPJ ጋዜጠኛዉ የበረካታ ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ እስረኞችን የፍርድ ሒደት እንዲሁም በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰዉን ተቃዉሞ ሲዘግብ መቆየቱን አዉስቷል. ይኸዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ ጋዜጠኛዉ ለእስር የተዳረገበትን ምክንያት ለማወቅ ለመንግስት ባለስልጣናት ጥያቄን ቢያቀርብም ምላሽ አለማግኘቱን አስታዉቋል. በአዲስ አበባ ማዕከላዊ የምርመራ እስር ቤት ምርመራ እየተካሄደበት የሚገኘዉ የነገር-ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ምርመራዉ ከተጠናቀቀ በኋላ በተለመደዉ የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ሊመሰረትበት እንደሚችል CPJ ባወጣው መግለጫው አመልክቷል. ሰማያዊ ፓርቲ ለንባብ በሚያበቃዉ ነገር-ኢትዮጵያ ላይ በዋና አዘጋጅነት ሲያገለግል የነበረዉ ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፈራዉ በአሁኑ ወቅት በማንም እንዳይጎበኝ ተደረጎ እንደሚገኝምታውቋል. ባለፈዉ ሳምንት በኦሮሚያ ራዲዮና ቴሌቭዥን ጣቢያ በማገልገል ላይ የነበረዉ ጋዜጠኛ ፍቃዱ ምርቃና ለእስር መዳረጉ ይታወሳል. ይህ በእንዲህ እንዳለ ከወራት በፊት ከተመሰረተባቸዉ ክስ በነጻ የተሰናበቱት አምስት ጦማርያን ከነገ-በስትያ ረቡዕ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መጠራታቸዉን አሳስቦት እንደሚገኝ CPJ ሰኞ አክሎ ገለጿል. ከሳሽ አቃቤ ህግ ጦማሪያኑ በነጻ እንዲሰናበቱ የተላለፈዉን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ እንደሚያቀርብ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን የጦማሪያኑ ክስም በድጋሚ ሊታይ ይችላል ተብሎ መጠበቁን ከሀገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል. በአሁኑ ወቅት ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ በሶስተኛ ደረጃ ላይ በምትገኘዉ ኢትዮጵያ 10 ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገው እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል.

posted by Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: