አል ሲሲ ዜጎቻቸውን ‹‹ በኢትዮጵያ ግድብ ስጋት አይግባችሁ››ብለዋል

የግብጹ ፕሬዘዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ዛሬ ለአገራቸው ህዝብ በኢትዮጵያው የህዳሴው ግድብ ዙሪያ ስጋት እንዳይገባቸው በመግለጽ ‹‹ነገሮች ጥሩ እየሄዱ ነው››ብለዋል፡፡
‹‹ውሃ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ የግብጻዊያንን ስጋት ሙሉ ለሙሉ እገነዘባለሁ››በማለት ፕሬዘዳንቱ የተናገሩት በፋራፍራ አካባቢ የአገሪቱን ለእርሻ የሚውል መሬት ለማስፋት በተዘጋጀ ብሄራዊ ፕሮጀክት የምረቃ ስነስርዓት ላይ ነው፡፡
ሲሲ ‹‹ ከወንድሞቻችን ኢትዮጵያዊያን ጋር ተስማምተናል፡፡እኛ መኖር እንደምንፈልገው እነርሱም መኖር ይፈልጋሉ፡፡ከዚህ በፊት ወደ ውድቀት አልመራኋችሁም አሁንም ወደ ውድቀት አልመራችሁም ››በማለት ግብጻዊያን በዚህ ጉዳይ እንዲተማመኑባቸው ጠይቀዋል፡፡
የፕሬዘዳንቱ ንግግር የካርቱሙ ድርድር በስምምነት እንደተጠናቀቀ በተገለጸ 24 ሰዓታት ውስጥ የተደመጠ ነው፡፡ካይሮ በተደጋጋሚ ጊዜያት ኢትዮጵያ በመገንባት ላይ የምትገኘው ግድብ ወደ ግብጽ ይደርስ የነበረውን የውሐ መጠን ሊቀንሰው ይችላል በማለት ስትገልጽ ቆይታለች፡፡ኢትዮጵያ በበኩሏ ግድቡ የታችኞቹን የተፋሰስ አገራት አይጎዳም በማለት የግብጽን አቤቱታ ስታጣጥል ቆይታለች፡፡የዜናው ምንጭ አህራም ኦን ላይን ነው፡፡

Dawit Solomon Yemesgen's photo.posted by Aseged Tamene
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: