ሱዳን ፣ግብፅና ኢትዮጵያ በካርቱም ሲያደርጉ የቆዩትን የሶስትዮሽ ውይይት በስምምነት ማጠናቀቃቸው ተሰምቷል

ሱዳን ፣ግብፅና ኢትዮጵያ በካርቱም ሲያደርጉ የቆዩትን የሶስትዮሽ ውይይት በስምምነት ማጠናቀቃቸው ተሰምቷል ።የውይይይቱን ማዕቀፉችን ስምምነት ያረፈባቸውን ነጥቦች ሳይጠቅሱ አንዳንድ ኮካዎች የባድመን ተወሰነችልን ሊደግሙብን ዳር ዳር እያሉ ነው ።
ከካርቱም የወጡ መረጃዎች እንደጠቆሙት ከሆነ ስምምነት የተደረሱባቸው ነጥቦች በአብዛኛው ግብፃውያንን ጮቤ ያስረገጡ ሆነዋል ።
1)በማርች ወር የሶስቱ አገራት ፕሬዝዳንቶች ያፀደቁትን ደንብ በስራ ላይ ለማዋልናአስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ደንቡን ለመሰረዝ ተስማምተዋል ።ግብፅ ኢትዮጵያ የፈረመችውን ደንብ እያከበረች አይደለም በማለት ስሞታ ስታቀርብ መቆየቷ አይዘነጋም ።
2) በግድቡ ዙሪያ የሚደረገው ጥናት በስምንት ወራት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ።ይህም በቅርብ ግዜ ውስጥ ግድቡ በተወሰነ ደረጃ ውሃ ተሞልቶ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ይጀምራል ሲሉ ለነበሩ መልካም ዜና አይደለም ።
3) አጨቃጫቂ ሆኖ የቆየው አዲስ አጥኚ ቡድን መቅጠር የግብፅ ተደራዳሪዎችን ባስደሰተ መልኩ እልባት በማግኘቱ በሆላንዳዊው ካምፓኒ ቦታ ሌላኛው የፈረንሳይ አጥኚ ካምፓኒ አርቴርሊያ ተተክቷል ።በሆላንዳዊው ካምፓኒ ደስተኛ ያልነበሩት ግብፁች እሰይ ስለቴ ሰመረ ማለት ጀምረዋል ።
የግብፁ አቡ ዛኢድ ስለዛሬው ስምምነት ለአገራቸው ሚዲያ “የዛሬው ሁኔታ ካለፉት ጊዜያት የተሻለ ነው “ብለዋል ።
4) ግብፅ ለታችኛዎቹ የተፋሰስ አገራት ከግድቡ የሚወጣው ውሃ የቀድሞ መጠኑን ሳይቀንስ እንዲወርድ የግድቡ በሮች ብዛት እንዲኖራቸው መጠየቋን ተከትሎ ኢትዮጵያ በቀጣዩ ሳምንት የቴክኒክ ምክክር ለማድረግ ተስማምታለች ።
5)የውይይቱ ዋነኛ መከራከሪያ የነበረውም ኢትዮጵያ ለአምስት ተከታታይ አመታት ግድቡን በውሃ ለመሙላት መዘጋጀቷን መናገሯ ነበር ።ግብፅ ውሃ መሙላቱ ቢያንስ ለስምንት ወራት የተቀጠረው የጥናት ቡድኖቹ ሪፖርት እስኪቀርብ እንዲዘገይ በመጠየቅዋ ውሃ መሙላቱ ይዘግይ ተብሏል ።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: