በጎንደሩ የህወሓት አገዛዝ ግዙፍ ወህኒ ቃጠሎ ምክንያት ያመለጡ እስረኞችን በማደን ላይ የነበሩት ፖሊሶችና ሚሊሻዎች ጥቃት ተፈፀመባቸው፡፡

d2256-amharademocraticmovementforce-ethiopia2

የህወሓት አገዛዝ ፖሊሶችና ታጣቂዎች በአምባ ጊዮርጊስ ጀጀሆ ከፍተኛ አሰሳና የቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ የአካባቢውን ነዋሪ ሲያስጨንቁ የሰነበቱ ሲሆን በመጨረሻም አንድን የጦር መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ ግለሰቡ ድንገት በከፈተባቸው ተኩስ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ግለሰቡም ገድሎና አቁስሎ ለመሰወር ችሏል፡፡
በግለሰቡ ከተገደሉት ታጣቂዎች መካከል አስማማው ሀብቴ የተባለው ሲገኝበት አስከሬኑ በጭልፎ ወንዝ ባለእግዚአብሄር ተቀብሯል፡፡ መኩሪያው የተሰኘው ፖሊስ ደግሞ በጠና ቆስለው የመዳን ተስፋ ከሌላቸው መካከል አንዱ ነው፡፡
በህዳር ወር መገባደጃ ላይ በጎንደሩ የህወሓት ወህኒ በተነሳው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ምክንያት በርካታ እስረኞች ማምለጣቸውና በጥይት መጨፍጨፋቸው አይዘነጋም፡፡

posted by Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: