የአማራን መገፋት ያመነው የትምክህተኛው ወያኔ ሰነድ

የሚከተለው ሰነድ ሰሞኑን ለከፍተኛ አመራሮች እየተሰጠ ያለ ሲሆን ከአዲስ አበባ በዛሬው እለት የተላከልን ነው፡፡ ሰነዱ የአማራን ከየክልሉ መባረር እውቅና ይሰጣል፡፡ ማእከላዊ ጭብጡ አማራ ነው፡፡ ትምክህተኛው፤ የድሮ ስርአት ናፋቂው፤ የነገስታቱ ስርአት ደቡብን እና ኦሮሚያን እንደበደለ፤ የትምክህት ሀይሉ የድሮ ስርአት ለመመለስ እንደሚጥር ይወቅሳል፡፡ አማራው በሌሎች ክልሎች የሌሎችን ብሄሮች ቋንቋ ካወቀ ለፖለቲካ ምርጫ ሊደርስ እንደሚችልም በማተት ያሾፋል፡፡ አማራ ከየክልሉ የሚባረረው ሌሎችን ስለሚንቅ ነው በማለት አገርን ያህል ነገር የናቅከኝ ገላመጥከኝ የልጆች ጨዋታ ያስመስለዋል፡፡ በአማራው ላይ የሚደርሱትን በደሎች የትምክህት ሀይሉ በማጋነን የብሄር ግጭት ለማስነሳት እንደሚጥር ያትታል፡፡ በሌላ በኩል አማራን ማባረር የተቀደሰ ተግባር እንደሆነ ይለፍፋል፡፡ እንጨት ስለሚቆርጡ እና የተፈጥሮ ሚዛን ስለሚያዛቡ በመሆኑ ሰብአዊ መብታቸው ተጠብቆ እንደተባረሩ በማተት ያላግጣል፡፡ በሚገርም ሁኔታ ከክልላቸው ውጭ የሚኖሩ አማሮች ሁለት ሚሊዮን መሆናቸውን ይናገራል፡፡ በተጨባጭ 10 ሚሊዮን አማራ ከክልሉ ውጭ እንደሚኖር እየታወቀ ይህ ሰነድ ግን ሁለት ሚሊዮን ናቸው ይላል፡፡ በዚህም በቀጣይ ጥቂት አመታት 8 ሚሊዮን አማራ አባሮና ገድሎ የማጥፋት እቅዱን በዘወርዋራ መንገድ ይፋ አድርጓል፡፡ የትምክህት ሀይሉ የትግራይ የበላይነት እንዳለ በማስመሰል የአገሪቱን እኩላዊ ስርአት ያጥላላል ሲልም ይከሳል፡፡ በጠቅላላው ሰነዱ አንድ አገርን እመራለሁ በሚል አካል የተጻፈ ሳይሆን ገፋሀኝ አየኸኝ ብለው የሚጣሉ መሸተኞችን ለመዳኘት የቆመ ነው የሚመስለው፡፡ ቤተ አማራም ለትምክህተኛው ወያኔ እንዲህ ከማድበስበስ እና ከመዛበር የአማራን ህዝብ ይፋዊ ይቅርታ ቢጠይቅና አማራው ላይ ለደረሰበት ማናቸውም በደል ካሳ ቢከፍል የተሻለ ይሆናል ብላ ትመክራለች፡፡ ከዛ ውጭ ያለው መዛበር ቀናቸውን ያስመሽ ይሆን እንደሁ እንጅ ፋይዳ የለውም፡፡ 

Melek Hara's photo.
Melek Hara's photo.
Melek Hara's photo.
posted by Aseged Tamene
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: