“የ25 ሚሊየን ብር ሙስና በደብረ ማርቆስ ከተማ ከንቲባ (አቶ ደረጀ)

በደብረ ማርቆስ ከተማ መንቆረር የሚባል በድሃው ህዝብ ሀብት የተቋቋመ የኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አለ። ነገር ግን ይህ ድርጅት በተወሠኑ ሃላፊዎችና ሙሰኞች የሚንቀሣቀስ ነው። እንደሚታወቀው ካጅማ የተባለ የውጭ ድርጅት ከደጀን እስከ ደብረ ማርቆስ ከተማ ደረጃውን ያልጠበቀ አስፓልት ገንብቶ ጨርሷል። እንዲሁም ይህ የውጭ ድርጅት ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን መሣሪያዎች ያውም መለዋወጫ የሌላቸው ማሽኖችን ማለትም የድንጋይ መፍጫ ክሬሸር ከመንቆረር ኢንተርብራይዝ ጋር በአቶ ደረጀ እና በአቶ ዳንኤል ደላላነት አማካኝነት ከካጅማ ሰራተኛ ከሆኑት የውጭ ዜጎች ጋር በመመሣጠር ይህን ያረጀ ማሽን በ25 ሚሊየን ብር ለመግዛት አዲስ አበባ በሚገኘው የካጅማ ቢሮ በዚሁ ሣምንት በሚስጥር ተፈራርመዋል። የድሃው ህዝብ ሃብት በነዚሁ ሙሰኛ ሃላፊዎች ትብብር ያውም በውጭ ዜጋ የድሃው ህዝባችን ሃብት እየተመዘበረ ይገኛል። ከአንዱ የውጭ ዜጋ ማለትም ከካጅማ ሰራተኛ ከሆነው ኢንጂነር እንደሰማነው ከሆነ የከተማው ከንቲባ የሆኑት አቶ ደረጀ 3 ሚሊየን አምስት መቶ ሺ ብር እንዲሁም አቶ ዳንኤል 3 ሚሊየን አምስት መቶ ሺ ብር ፈርቅ በመያዝ በ 25 ሚሊየን ብር እንደተገበያዩ አድርገው ብር ተቀብለዋል። ስለዚህ ይህን ጉዳይ የሚመለከተው አካል በአፋጣኝ አጣርቶ እነዚህን ሙሰኞች ለህግ እንዲያቀርባቸው እንጠይቃለን።

ድል ለድሃው ህዝባችን!!!

posted by Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: